BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሎ በፓርላማ

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች፣ ወርኃ ጥርን ያገባደዱት ሕግ በማውጣት አልያም ተቋማትን በመቆጣጠር እና የመስክ ጉብኝት በማድረግ ብቻም አልነበረም፤ ከዚያ አለፍ ብለውም፣ የአገሪቷ ርዕሰ-መንግሥት የዚኽኑ በጀት ዓመት የመንፈቅ የሥራ አፈጻጸም በማድመጥ እና ከሪፖርቱም ሻገር ያሉ ማኅበረ-ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲ ተኮር ጥያቄዎችን አንስተው ምላሽ እንዲሰጧቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመጠየቅም ነበር። እንደራሴዎቹ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል፤ ከሰላም እና ጸጥታ እስከ የተፈናቃዮች አኹናዊ ኹኔታ፣ […]

የብሪጅ ዳሰሳዊ ምልከታ፣ በሽግግር ፍትሕ፣ በእንደራሴዎቹ ሚና እና ተያያዥ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ

        የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ከኹለት ዓመታት በፊት አንድ ግዙፍ ፖሊሲ አጽድቆ ነበር። ይኽ የሽግግር ፍትሕ የተሰኘው የበዙ ማኅበረ-ፖለቲካዊ እና ተቋማዊ ተጽዕኖዎች ያሉት ፖሊሲ፣ ምንም እንኳን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካጸደቀው ዋለ አደር ቢልም፣ አልፎም የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ-ካርታው ነሐሴ 2016 ዓ.ም. በፍትሕ ሚኒስቴር አማካኝነት ቢዘጋጅም፣ ትግበራው የመዘግየት ኹኔታ […]