We are a non-profit think tank and Parliamentary Monitoring Organization specializing in parliamentary affairs and the sub-regional organization of the Intergovernmental Authority on Development (IGAD). Established and registered in December 2024 in Addis Ababa, Ethiopia, it operates as a local organization in accordance with the FDRE Civil Society Organization Proclamation No. 1113/2019.
ግንቦት 24 2018 ዓ.ም. በተደረገው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ የፌደራሉን (547 መቀመጫዎች) ጨምሮ የ12 ክልሎች እና የኹለት ከተማ መሥተዳድሮች ምክር ቤቶች (2,916 መቀመጫዎች) በአጠቃላይ ለ14 የሕግ አውጪ ምክር ቤት መቀመጫዎች ላይ ምርጫ ተከናውኗል። በአኹኑ ወቅት ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የሰጣቸው 24 አገር አቀፍ እና 45 የክልል ፓርቲዎች የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚኽ ውስጥም 42ቱ ፓርቲዎች የመራጮችን ድምፅ ለማግኘት በምርጫው ላይ ፉክክር አድርገዋል። ያም ሆኖ በአማራ ክልል በ8 እና በትግራይ ክልል በ38 (በድምሩ በ46) የምርጫ ክልሎች ውድድሩ ባለመካሄዱ በቀጣዩ መስከረም መጨረሻ የሚመሰረተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ501 መቀመጫዎች ሥራውን ይጀምራል። ይኽ ኹኔታ የምክር ቤቱን ምሉዕ የፌዴሬሽኑን ተዋጽዖ በጊዜያዊነት ገድቦት ቢቆይም፣ የሕግ አውጪነት ሕጋዊ ቅቡልነቱን ግን አያግደውም።
በሌላ በኩል፣ ሕግ የማውጣት ሳይሆን ሕገ-መንግሥትን የመተርጎም እና ብሔረሰቦችን የመወከል ሥልጣን ያላቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የሦሥቱ አዳዲሶቹ ክልሎች የብሔረሰቦች ምክር ቤቶች ምርጫ በዚኽ ወቅት ባይካሄድም፣ ከቀድሞው የደቡብ ክልል ወጥተው ራሳቸውን የቻሉት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ለመጀመሪያ ጊዜ በዚኽ ጠቅላላ ምርጫ መሳተፋቸው የክልላዊ ፌዴራሊዝም ተቋማዊ ሽግግራቸውን የሚያጠናክር ትልቅ መሠረት ይሆኗል።
ካለው ሥርዓታዊ እና ፖለቲካዊ ነባራዊ ኹኔታ አኳያ የብሪጅ ምልከታ እንደሚያሳየው፣ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ለብቻው የተወዳደረባቸውን 65 መቀመጫዎች ጨምሮ በብዙዎቹ የክልል ምክር ቤቶች ከ50 በመቶ በላይ ወንበሮችን በቀላሉ ሊያሸንፍ እንደሚችል እና በቀጣዩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም መንግስት የመመሥረት አብላጫ ድምፅ እንደሚያገኝ ይገመታል። ከተቀመጡት 501 ወንበሮች መካከል ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነውን መቀመጫ ይይዛሉ የሚለው የተቋማችን የቢሆናል መላምት ቢሳካ፣ ይኽ ውክልና በፓርላማው ውስጥ የፖሊሲ ክርክሮችን ለማነቃቃት እና የመንግስትን የሥራ አሥፈጻሚ ተቋማትን የመቆጣጠር ሚናን ለማሳደግ ጠቃሚ አቅም ይፈጥራል።
This research report is published by the House of Peoples Representatives (HoPR) of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE), BRIDGE Research and Innovation for Democratic Governance and Enhanced Peace (BRIDGE), and with the support of the Netherlands Institute for Multiparty Democracy (NIMD). It was conceptualized and written by BRIDGE and reviewed by an HoPR team of MPs and HoPR Secretariat Staff.
Location: Kirkos Sub-city, Woreda 08, Kazanchis, across the main gate of UNECA, SA Building, 9th Floor, Office No. 5, Addis Ababa.
Address: Email: info@bridge-et.org,
Office: +251 115 57 74 96,
Mobile: +251998085013,
P.O. Box: 150096, Addis Ababa, Ethiopia.