የክልሉ ም/ቤት አወቃቀርና፣ አወካከል፤ ሥልጣንና ተግባር
አንቀጽ 48
የሐረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት
የሐረሪ ሕዝብ ክልል ም/ቤት 36 አባላት ያሉትና በሁለት ጉባኤዎች የተወቀረ የክልል ም/ቤት ነው፡፡
አንቀጽ 49
የም/ቤቱ ጉባኤዎች
ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤና
ለ/ የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ናቸው
አንቀጽ 50
የጉባኤዎች አከፋፈል አወካከልና አመራረጥ
አወካከሉ፡-
ሀ/ ከጆገል ምርጫ ክልል 4 አባላትና
ለ ከጆገል ውጭ ካሉት የከተማ ቀበሌዎችና የገጠር ቀበሌ ገበሬ ማህበራትን የሚያጠቃልል የምርጫ ክልል 18 አባላት ይመረጣል፡፡
ክፍል አንድ
ስለ ክልሉ ምክር ቤት
አንቀጽ 51
የሐረሪ ሕዝብ ክልል ም/ቤት ሥልጣንና ተግባር
ሀ/ የክልሉን ሕገ- መንግስትና ሌሎች ሕጎችን ያወጣል፡፡
ለ/ በዚህ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 79 በተደነገገው መሠረት የክልሉን ሕገ- መንግስት ያሻሽላል፡፡
ሐ/ የፌደራል ሕገ- መንግስት ለክልሎች የተሰውን ስልጣን በክልሉ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
መ/ ለክልሉ ኘሬዚዳንት በሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ጠቋሚት የሚቀርበውን እጩ በ2/3ኛ ድምጽ መርምርሮ ይመርጣል፡፡
ሠ/ የክልሉን የውስጥ አስተዳደር ያዋቅራል ያደራጃል፡፡
ረ/ የክልሉን የሕዝብ ደህንነትና ፀጥታን በሚመለከት ሕጎች ደንቦችና መመሪያዎት ያወጣል
ሰ/ የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤና በክልሉ መስተዳደር ም/ቤት የሚቀርቡለትን አዋጆች ደንቦች መመሪያዎችና ፖሊሲዎች መርምሮ ይፀድቃል፡፡
ሸ/ በክልሉ ኘሬዚዳንት የቀረቡትን ም/ኘሬዚዳንት የክልል አስፈፃሚ/ካብኔ/ አባል የሆኑ የቢሮ ኃላፊዎትና ሌሎች ተመሳሳይ ስልጣን ያላቸውንና ኃላፊዎች ሹመት ያፀድቃል፡፡
ቀ/ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ኘሬዚዳንት ምክትል ኘሬዚዳንትና ዋና ኦዲተር እና የፖሊስ ኮምሽነር ይሾማል።
በ/ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሚቀርቡበትን ዳሄት ሹመት ያፀድቃል፡፡
ተ/ የክልሉን የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ፣ ደንብና መመሪያ የወጣል፡፡
ቸ/ ለክልሉ በተሰጠው የገቢ ምንጭ ወሰን ግብርና ታክስ ይጥላል፡፡
ነ /የክልሉን አመታዊ በጀት ይፀድቃል፡፡
ኘ/ በክልሉ ውስጥ ማናቸውም ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋ ሲየጋጥም ወይምየሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥጭ በሸታ ሲከሰት የአስቸኩይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፡፡
አ/ የክልሉን መንግስት የገቢ ምንጮች የሚመለከቱ ሀጎች ያወጣል፡፡
ወ/ በህጉ መሰረት ምህረት ያደርጋል፣ የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ መመሪዎችን ያወጣል፡፡ የፀጥታና የፖሊሲ ሃይሉን ያቋቁማል
የ/ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ሌሎች የክልሉን መንግስት ባለስልጣናት ለጥየቄ ይጠራል የአስፈፃሚዉን አካል አሠራር ይመረምራል፡፡
አንቀጽ 52
የም/ቤቱ አመራርና አሠራር
አንቀጽ 53
የአፈ–ጉባፌው ስልጣንና ተግባር
1.የም/ቤቱን መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎች ይጠራል፡፡ ይመራል፡፡
አንቀጽ 54
የምክትል አፈ–ጉባኤው ስልጣንና ተግባር
አንቀጽ 55
የም/ቤቱ አባላት መብትና ግዴታ
አንቀጽ 56
የም/ቤቱ የስብሰባ ጊዜና የሥራ ዘመን
አንቀጽ 57
የውሳኔ አሰጣጥና የአሰራር ሥነ–ሥርዓቶች
ክፍል ሁለት
የጉባኤዎች ስልጣንና ተግባር
አንቀጽ 58
የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ ስልጣንና ተግባር
የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ በክልል ም/ቤት ከሚኖረው ስልጣንና ተግባር በተጨማሪ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር በተጨማሪ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡
Location: Kirkos Sub-city, Woreda 08, Kazanchis, across the main gate of UNECA, SA Building, 9th Floor, Office No. 5, Addis Ababa.
Address: Email: info@bridge-et.org,
Office: +251 115 57 74 96,
Mobile: +251998085013,
P.O. Box: 150096, Addis Ababa, Ethiopia.