የብሪጅ ዳሰሳዊ ምልከታ፦ የፓን አፍሪካው ፓርላማ፣ እንዴት-ወዴት?

በአፍሪካ ኅብረት ሥር የሚገኘው አህጉራዊው የፓን አፍሪካ ፓርላማ፣ ከሚያዝያ 28 እስከ 30 ድረስ፣ መቀመጫው በሆነው በደቡብ አፍሪካዋ ሚድራን ከተማ ባካሄደው ሰባተኛው ጉባኤው፣ ፕሬዝደንቱን እና ምክትል ፕሬዝደንቶቹን መርጧል። በዚያ የሦሥት ቀናት ጉባኤውም ከመረጣቸው ምክትል ፕሬዝደንቶቹ መካከል፣ የኢትዮጵያው እንደራሴ የተከበሩ ዶ.ር. አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል። የተከበሩ ዶ.ር. አሸብር፣ በዚኽ የአመራር ቦታቸውም፣ የምሥራቅ አፍሪካን […]
የብሪጅ ዳሰሳዊ ምልከታ፦ ሰው ሠራሽ አእምሮ በኢትዮጵያ፦ ተግዳሮቶች እና ተስፋዎች

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በወርኃ ሚያዚያ በእንደራሴዎቹ ምክር ቤት ተገኝተው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ካቀረቡት የፌደራል ተቋማት መካከል አንዱ ነበር። ኢንስቲትዩቱ ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል። ከተጠቀሰው የተቋሙ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በተጨማሪ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር. ዐቢይ አህመድ በአህጉሪቱ ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማሳደግ ረገድ ላሳዩት አመራር እውቅና […]
የብሪጅ ዳሰሳዊ ምልከታ፦ የሲቪል ማኅበረሰብ በኢትዮጲያ ከየት ወዴት

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ በወርኃ ሚያዚያ ከከወናቸው ሕገ-መንግሥታዊ ኅላፊነቶች መካከል አንዱ፣ የፌደራል ተቋማትን የዚኽን በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም መገምገም ነበር። ወደ እንደራሴዎቹ አዳራሽ ተጠርተው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ካቀረቡት ተቋማት መካከልም፣ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን በጊዜ ምጣኔ ቀዳሚው ነበር። በእንደራሴዎቹ ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የተቋሙን ሪፖርት ማድመጡ ሲዘገብ፣ ባለሥልጣኑም፣ በሲቪል […]