የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ወርኃ ግንቦትን ያጠናቀቀው፣ ተለምዷዊዎቹን ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹ የሆኑትን ሕግጋት ማውጣት፣ ሥራ አሥፈጻሚ ተቋማትን መቆጣጠር እና የአሥረጂ መድረኮችን ከማካሄድ ባለፈ፣ የተወሰኑ የተቋማት ጉብኝቶችን እና ፓርላመንታዊ ዲፕሎማሲዎችንም ከውኗል። ይኽች የግንቦት የእንደራሴ ዕትምም፣ እኒኽን ርዕሰ-ጉዳዮች እና ለወሩ መገባደጂያ ይሆናል ብላ የመረጠችውን ዳሰሳዊ ምልከታዋን አካታ እንዲኽ ተዘጋጅታለች።