...

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ በወርኃ ሚያዚያ የተለያዩ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን አከናውኗል። ከእነዚኽ ዋንኛ ኃላፊነቶቹ መካከልም፣ ሕግጋትን ማጽደቅ፣ የሥራ አሥፈፃሚ ተቋማት ሪፖርቶችን ማድመጥ፣ ፓርላመንታዊ ዲፕሎማሲዎችን መከወን እና የተቋማት እና የመስክ ጉብኝቶችን ማድረግ የወሩ የምክር ቤቱ አበይት ክንውኖች ነበሩ። ይኽች የእንደራሴ ዐሥራ አምስተኛ ዕትምም፣ እኒኽን ጉዳዮች በመልክ በመልካቸው አጠናቅራ እና ለወሩም እንዲሆን አንድ የብሪጅ ዳሰሳዊ ምልከታን አካታ እንዲኽ ተጠናቅራለች።

Seraphinite AcceleratorOptimized by Seraphinite Accelerator
Turns on site high speed to be attractive for people and search engines.