BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

  1. Home
  2. /
  3. Publications
  4. /
  5. ወርኃዊ ጥንቅር፣ ቁ. 011 ታኅሣሥ  2018...

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ በወርኃ ታኅሣሥ የተለያዩ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን አከናውኗል። ከእነዚኽ ዋንኛ ኃላፊነቶቹ መካከልም፣ ሕግጋት ማውጣት፣ የሥራ አሥፈፃሚ ተቋማት ሪፖርቶችን ማድመጥ፣ ፓርላመንታዊ ዲፕሎማሲ፣ የፌደራል ተቋማትን መጎብኘት እና የመስክ ጉብኝቶችን ማድረግ የወሩ የምክር ቤቱ አበይት ክንውኖች ናቸው። ከዚኽ በተጨማሪም፣ ሦሥት የፌድራሉን ሚኒስትሮች ወደ አዳራሹ ጠርቶ፣ ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ባላቸው ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን አንስቶ፣ የሚኒስትሮቹን ምላሾችን ሲያደምጥ፤ የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስትርን ታሪካዊ ንንግሮች አድምጧል። ይኽች የብሪጅ ዐስራ አንደኛ ዕትምም፣ እነዚኽን የምክር ቤቱን የታኅሣሥ ክራሞት ጨምሮ፣ የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግር ተንተርሳ ያዘጋጀችውን ዳሰሳ አክላ እንዲኽ ተጠናክራለች።