ወርኃዊ ጥንቅር፣ ቅጽ 02 ቁ. 014 መጋቢት 2018 ዓ.ም እንደራሴ

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ በወርኃ መጋቢት የተለያዩ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን አከናውኗል። ከእነዚኽ ዋንኛ ኃላፊነቶቹ መካከልም፣ ሕግጋትን ማጽደቅ፣ የሥራ አሥፈፃሚ ተቋማት ሪፖርቶችን ማድመጥ፣ ፓርላመንታዊ ዲፕሎማሲዎችን መከወን እና የመስክ ጉብኝቶችን ማድረግ የወሩ የምክር ቤቱ አበይት ክንውኖች ነበሩ። ከዚያ ባለፈ ከሐምሌ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ከሚያካሂዱት የውክልና ሥራ በተጨማሪ፣ ከየካቲት የለጠቀውን የውክልና ሥራቸውን አከናውነዋል። ከዚኽ አኳያም፣ በዚኹ ወርኃ መጋቢት […]
ወርኃዊ ጥንቅር፣ ቅጽ 02 ቁ. 013 የካቲት 2018 ዓ.ም እንደራሴ

ጤና ይስጥልን ክቡራትን እና ክቡራን የእንደራሴ ሰዎች፣ እነሆ እንደራሴ ብለን የሰየምናት የእንደራሴዎቹን ወርኃዊ ክራሞት የምትተነትነው መጽሔታችን፣ አንዱን ዓመት አጠናቃ ወደ ኹለተኛ ዓመቷ መሻገሯን ስናብስራችኹ እጅጉን በሀሴት ነው። ያለፉትን ዐሥራ ኹለት ዕትሞች ስላነበባችኹልን፣ አስተያቶቻችኹንም ስለለገሳችኹን እጅ እንነሳለን። የጎደሉትን እየሞላን፣ የበረታንባቸውንም እያጠናከርን ኹለተኛ ቅጻችንንም በየወቅቱ እንደምናደርሳችኹ ቃላችንን እንካችኹ። እናመስግናለን። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች፣ በወርኃ የካቲት ተለምዷዊ […]
ወርኃዊ ጥንቅር፣ ቁ. 012 ጥር 2018 ዓ.ም እንደራሴ

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች፣ በወርኃ ጥርም የተለያዩ ሕገ-መንግሥታዊ እና ተቋማዊ ኅላፊነቶቻቸውን ከውነዋል። በወሩ ውስጥ ሦሥት መደበኛ ስብሰባዎችን ሲያደርጉ፣ የአገሪቷን ርዕሰ-መንግስት የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ተከትሎ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና ማብራሪያ ያሻቸዋል ያሏቸውን አገራዊ ጉዳዮች አንስተው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሾች አድመጠዋል። ከዚያ ባለፈም፣ ዐዋጆችን አጽደቀዋል፤ ረቂቅ ሕግጋትንም ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርተዋል። ይኽች የእንደራሴ የቅጽ አንድ የመጨረሻ ዕትምም፣ […]