BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

የተሻሻለው የ1994 ዓ/ም የሶማሌ ክልል ሕገ-መንግስት

ክልል ምክር ቤት

አንቀጽ 48

ስለ ክልሉ ምክር ቤት

  1. የክልሉ ምክር ቤት አባላት ሀሉ አቀፍ ነፃ ፣ ቀጥተኛ ፣ ትክክለኛ በሆነና ድምጽ በሚስጥር በሚጥበት የምርጫ ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ ይመረጣሉ፡፡
  2. የክልሉ ምክር ቤት አባለት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሌች ተወዳዳሪመት መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡
  3. የክልሉ የምክር ቤት አባላት የመላው ክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ናቸው፡፡

ተገዥነታቸውም፣

ሀ/ ለሕገ-መንግስቱ

ለ/ ለህዝቡና

ሐ/ ለራሳቸው ህሊና ብቻ ይሆናል፡፡

  1. ማንኛውም የክልል ምክር ቤቱ አባል በምክር ቤቱ ስብሰባ በሚሰጠው ድምጽ ወይም አስተያየት ምክንያት አይከሰስም፣ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወስድበትም፡፡
  2. ማንኛውም የክልሉ ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፡፡ በወንጀል አይከሰስም፡፡
  3. ማንኛም የክልሉ ምክር ቤት አባል የመረጠው ህዝብ አመኔታ ባጣበት ጊዜ በህግ መሠረት ከምክር ቤት አባልነት ይወገዳል፡፡

አንቀጽ 49

የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር

  1. የክልሉ ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግስት መሠት የክልሉ ሕግ አውጭ አካል ነው፡፡
  2. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪበፑብሊ ሕገ-መንግስት እንደጠበቀ ሆኖ የክልሉ ምክር ቤት በክልሉ የውስጥ ጉዳዮች ላይ የበላይ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት ነው፡፡
  3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች ሥር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሉ ምክር ቤት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

ሀ/ በዚህ ሕገ- መንግስት መሠረት የፌደራሉ ሕገ-መንግስትና ሌሎች ሕጎችን የማጥፃረሩ ልዩ ልዩ ሕጎችን ያወጣል፡፡

ለ/ የሕዝቡን ብዛት፣ የክልሉን ስፋትና  ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት በክልሉ ውስጥ የአስተዳዳር እርከኖች ወይም የራስ በራስ አስተዳደራዊ አከባቢዎችን ያቋቁማል፡፡

ሐ/የፌደራል መንግስት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ከሌሎች ክልላዊ መንግስታት ጋር የሚደረገውን ስምምነት ያፀድቃል፡፡

መ/ ምክር ቤቱን የሚመሩ አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባዔ ይምርጣል፣ለምክር ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን ይሰይማል፡፡

ሠ/ ከምክር ቤቱ አባለላት መካከል ርዕሰ መስተዳድሩን በምርጫ ዳሰይማል፣ በርዕሰ መስተዳድሩና አቅራቢነት የክልሉን ካቢኔ ምክር ቤት አባላት ሹመት ያፀድቃል፤

ረ/ የኦዲትና የቁጥጥር አካል ያቋቁማል፡፡

ቀ/ የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የፀጥታና የፖሊሲ ኃይል ያቋቁማል፣

በ/ የክልሉን ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፤ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶችን ያፀድቃል፤

ተ/ የክለሉን መንግስት የገቢ ምንጮች የሚመለከቱ ሕጎችን ያወጣል፤ የክልሉን በጀት ያፀድቃል፤

ቸ/ የክልሉ በጀት የሚከፍፈልበትን ቀመር ይወስናል፤

ኀ/ ለማህበራዊ አገልግሎት መስፋፋትና ለኢካኖሚያዊ ልማት መፋጠን አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን ያቋቁማል፤ ያደራጃል፤

ነ/ በክልል ርዕሰ መስተዳድር አቅራቢነት የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት፤ ምክትል ኘሬዚዳንት እና ዋና ኦዲተሩን ይሾማል፤

ኘ/ ለክልሉ መንግስት በተከለለው የገቢ ምንጭ ግብርና ታክስ ይጥላል፤

አ/ የክልሉን የሠራተኛ አስተዳደርና  የስራ ሁኔታዎችና በተመለከተ ሕግ ያወጣል፤

ከ/ የሀገሪቱን ሕገ-መንግስት፤ አዋጆችና ሌሎች ሕጎች በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ደንቦችን የወጣል፤

ወ/ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች የክልሉን መንግስት አካላት ባለስልጣናት ለጥያቄ ይጠራል፤ የክልሉ የካቢኔ ምክር ቤት አሠራርን ይመረምራል፤

አንቀጽ 50

ስለ መክር ቤቱ አፈጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ አሰያየምና የስራ ዘመን

  1. የክልሉ ምክር ቤት የራሱ አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባፌ ይኖሩታል፤
  2. አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባኤው በዚህ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 3/መ/መሠረት አብላጫ ድምጽ ባገኘው የፖለቲካ ጉባኤው ተጠሪነቱ የክልሉ ምክር ቤት ነው፡፡
  3. የአፈ-ጉባኤው የሥራ ዘመን የክልሉ ምክር ቤት የሥራ ዘመን ይሆናል፡፡

አንቀጽ 51

የአፈጉባኤው ሥልጣንና ተግባር

የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የሚከተለሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡

  1. የምክር ቤቱን መደበኛና አስቸኩይ ስብሰባዎች ይጠራል፤ ይምራል፤
  2. መክርቤቱን በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወከላል፤
  3. የምክር ቤቱን ጽ/ቤት ያደራጃል፤ ጠቅላላ የአስተዳደር ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፤
  4. ምክር ቤቱ በአባሎቹ ላይ እንዲወሰድ የወሰነውን የዲሲፒሊን እርምጃወች ይፈድማል፤
  5. በክልሉ ምክር ቤት የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል፤

አንቀጽ 52

የምክትል አፈጉባዔው ሥልጣንና ተግባር

ምክትል አፈ-ጉባዔው ተጠሪነቱ ለአፈ-ጉባዔውና ለክልሉ ምክር ቤት ሆኖ፡-

  1. በአፈ-ጉባዔው ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
  2. አፈ-ጉባኤው በማይኖርበት ወይም ሥራውን ለማከናወን በማይቻልበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፤

አንቀጽ 53

ስለ ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት

  1. የክልሉ ምክር ቤት የራሱ ጽ/ቤት ይኖረዋል፤
  2. የጽ/ቤቱ ሥልጣንና ተግባር በህግ ይወስናል

አንቀጽ 54

የክልል ምክር ቤቱ የስብሰባ ጊዜና የሥራ ዘመን

  1. የክልሉ ም/ቤት ቢያነስ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፤
  2. የክልሉ ምክር ቤት አባላት የሥራ ዘመን ለአምስት ዓመት ነው፡፡ የሥራ ዘመኑ ከብቃቱ ከንድ ወር በፈት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ይጠናቀቃል፤ የቀድሞው የምክር ቤት የሥራ ዘመን በተጠናቀቀ በአንድ ወር ውስጥ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት ሥራውን ይጀምራል፤
  3. የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በማይኖርበት ወቅት አፈ-ጉባዔው አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ከንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቁ አፈ-ጉባኤው ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት፡፡
  4. የምክር ቤቱ ስብሰባ በግልጽ ይካሄዳል፤ ሆኖም ስብሰባው በዝግ እንዲካሄድ በአባለቱ ወይም በክልሉ የካቢኔ ምክር ቤት ከተየቀና ክክልሉ ምክር ቤቱ አባለት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ጥያቄውን ከደገፉት ዝግ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡

አንቀጽ 55

የውሳኔ አሰጣጥና የአሰራር ሥነሥርዓቶች

  1. ከከልል ምክር ቤት አባላት መካከል ከሁለተኛ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል፤
  2. ማናቸውም ውሳኔ የሚተላለፈው በክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በተገኙት አባላት አብላጫ ድምጽ ይሆናል፤
  3. መክር ቤቱ አሠራሩንና የህግ አወጣጥ ሂደቱን አስመልክቶ ዝርዝር ህጎችን ሊያወጣ ይችላል፤

አንቅጽ 56

የሀገር ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች ጉባኤን ስለማቋቋም

የሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች ጉባኤ በዚህ ሕገ-መንግስት ያቋቁማል ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤