ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም 190 አባላት ያሉት የሲዳማ ክልል ምክር ቤትከተመሠረተ በኋላ በዛኑ ቀን የክልሉን ሕገ መንግሥት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። አቶ ሰለሞን ላሌ የተመሠረተው የክልሉ ምክር ቤት የመጀመርያ አፈጉባኤ ሆነው ተመርጠው ነበር። በአሁኑ ወቅት ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ የሲዳማ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ናቸው፡፡