BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

ይህ አነስተኛ መጽሃፍ በፓርላማ እና ሕዝባዊ ተሳትፎ ላይ የተደረገ ጥናታዊ ጽሁፍ አካል ነው፡፡ ጥናቱ የተለያዩ ሒደቶችን፤ ማለትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የጽ/ቤቱን ሰራተኞች እና ባለሙያዎች በማነጋገር፣ የሕግ ማእቀፎችን እና ከፓርላማ ስራ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን በማየት፣ ብሎም በዘርፉ ላይ የተሠሩ ጥናቶችን በመመርመር ተከናውኗል፡፡ በይዘቱም፤ የኢትዮጲያን የሕግ እና የሕገ መንግስት ብሎም የፓርላማ ታሪክ፣ የኢፌድሪ ሕገ መንግስት አዋጣጥ ሒደት እና አሳታፊነት፣ የኢፌድሪ ፓርላሜንታዊ መንግስት አወቃቀር ሕግ የማውጣት ሒደት እና፣ በሒደቱም ሕዝባዊ ተሳትፎ ሊደረግ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች፣ “መረጃ” በሕግ ማውጣት ሒደት ውስጥ ከሚኖር ሕዝባዊ ተሳትፎ አንጻር ያለውን ቦታ፣ የምክር ቤት ውይይቶችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ስለማድረግ እና፣ ስለ ተሳትፎ መብት፣ ምንነትና ሒደት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ውይይቶች (Public Hearing)፤ መች፣ እንዴት እና ለምን ያህል ጊዜ መደረግ እንዳለባቸው፣ ብሎም የሲቪክ ማህበራት በሕግ ማውጣት ውስጥ ስለሚኖራቸውን ድርሻ – ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡