የሐረሪ ሕዝብ ክልል የተሻሻለዉ ሕገ መንግስት (1997)
የክልሉ ም/ቤት አወቃቀርና፣ አወካከል፤ ሥልጣንና ተግባር
አንቀጽ 48
የሐረሪ ህዝብ ክልል ምክር ቤት
የሐረሪ ሕዝብ ክልል ም/ቤት 36 አባላት ያሉትና በሁለት ጉባኤዎች የተወቀረ የክልል ም/ቤት ነው፡፡
አንቀጽ 49
የም/ቤቱ ጉባኤዎች
- የሐረሪ ሕዝብ ክልል ም/ቤት ሁለት ጉባኤዎች፡-
ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤና
ለ/ የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ናቸው
- የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤበዚህ ህገ መንግስት አንቀጽ 50/1/1 እንደመለከተው የሚወከሉ 14 የሐረሪ በሔረሰብ አባላት ይኖሩታል፡፡
- የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ በዚህ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 50/2/ እንደተመለከተው የሚወከሉ 14 የሐረሪ በሔረሰብ አባላት ይኖርታል
አንቀጽ 50
የጉባኤዎች አከፋፈል አወካከልና አመራረጥ
- የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ አባላት በሁለት የምርጫ ክልሎች የሚወከሉ አባላት ያሉት ጉባኤ ነው፡፡
አወካከሉ፡-
ሀ/ ከጆገል ምርጫ ክልል 4 አባላትና
ለ ከጆገል ውጭ ካሉት የከተማ ቀበሌዎችና የገጠር ቀበሌ ገበሬ ማህበራትን የሚያጠቃልል የምርጫ ክልል 18 አባላት ይመረጣል፡፡
- የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አባላት በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ በሌላ በኢትዮጽያ ከልሎችና ከተሞች ከሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ይመረጣል፡፡
- የጉባኤው አባለት ምርጫ ነፃና ቀጥተኛ በሆነ ድምጽ በሚስጥር በመስጠት ስርዓት ይፍጽማል
ክፍል አንድ
ስለ ክልሉ ምክር ቤት
አንቀጽ 51
የሐረሪ ሕዝብ ክልል ም/ቤት ሥልጣንና ተግባር
- የሐረሪ ሕዝብ ክልል ም/ቤት የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤና የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ በጋራ የሚሰበሰቡበት ም/ቤት ነው፡፡ በዚህ ህገ መንግስት መሠረት የክልሉ ህግ አውጪና በክልሉ የውስጥ ጉዳዮች ላይ የበላይ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤት ነው፡፡
- የሐረሪ ሕዝብ ክልል ም/ቤት የሚተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡
ሀ/ የክልሉን ሕገ- መንግስትና ሌሎች ሕጎችን ያወጣል፡፡
ለ/ በዚህ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 79 በተደነገገው መሠረት የክልሉን ሕገ- መንግስት ያሻሽላል፡፡
ሐ/ የፌደራል ሕገ- መንግስት ለክልሎች የተሰውን ስልጣን በክልሉ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
መ/ ለክልሉ ኘሬዚዳንት በሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ጠቋሚት የሚቀርበውን እጩ በ2/3ኛ ድምጽ መርምርሮ ይመርጣል፡፡
ሠ/ የክልሉን የውስጥ አስተዳደር ያዋቅራል ያደራጃል፡፡
ረ/ የክልሉን የሕዝብ ደህንነትና ፀጥታን በሚመለከት ሕጎች ደንቦችና መመሪያዎት ያወጣል
ሰ/ የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤና በክልሉ መስተዳደር ም/ቤት የሚቀርቡለትን አዋጆች ደንቦች መመሪያዎችና ፖሊሲዎች መርምሮ ይፀድቃል፡፡
ሸ/ በክልሉ ኘሬዚዳንት የቀረቡትን ም/ኘሬዚዳንት የክልል አስፈፃሚ/ካብኔ/ አባል የሆኑ የቢሮ ኃላፊዎትና ሌሎች ተመሳሳይ ስልጣን ያላቸውንና ኃላፊዎች ሹመት ያፀድቃል፡፡
ቀ/ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ኘሬዚዳንት ምክትል ኘሬዚዳንትና ዋና ኦዲተር እና የፖሊስ ኮምሽነር ይሾማል።
በ/ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሚቀርቡበትን ዳሄት ሹመት ያፀድቃል፡፡
ተ/ የክልሉን የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ፣ ደንብና መመሪያ የወጣል፡፡
ቸ/ ለክልሉ በተሰጠው የገቢ ምንጭ ወሰን ግብርና ታክስ ይጥላል፡፡
ነ /የክልሉን አመታዊ በጀት ይፀድቃል፡፡
ኘ/ በክልሉ ውስጥ ማናቸውም ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋ ሲየጋጥም ወይምየሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥጭ በሸታ ሲከሰት የአስቸኩይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፡፡
አ/ የክልሉን መንግስት የገቢ ምንጮች የሚመለከቱ ሀጎች ያወጣል፡፡
ወ/ በህጉ መሰረት ምህረት ያደርጋል፣ የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ መመሪዎችን ያወጣል፡፡ የፀጥታና የፖሊሲ ሃይሉን ያቋቁማል
የ/ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ሌሎች የክልሉን መንግስት ባለስልጣናት ለጥየቄ ይጠራል የአስፈፃሚዉን አካል አሠራር ይመረምራል፡፡
አንቀጽ 52
የም/ቤቱ አመራርና አሠራር
- ም/ቤቱ የራሱ አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባኤ ይኖሩታል፡፡
- እንደአስፈላጊነቱ ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ይኖሩታል፡፡
- አፈ-ጉባኤው በዝብ ተወዮች ጉባኤ በኩል እንዲሁም ምክትል አፈ-ጉባኤ በኩል እንዲሁም ምክትል አፈ-ጉባኤ በሐረነ በሔራዊ ጉባኤ በኩል ቀርበው በምክር ቤቱ በ2/3ኛ ድምጽ ይምረጣሉ፡፡
አንቀጽ 53
የአፈ–ጉባፌው ስልጣንና ተግባር
1.የም/ቤቱን መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎች ይጠራል፡፡ ይመራል፡፡
- የም/ቤቱን ጠቅላላ ሥራዎች ያስተዳድራል፡፡
- በም/ቤቱ አባላት ላይ የሚወሰኑ የዲሲፒሊን እርምጃዎችን ያስፈጽማል፡፡
- የአፈ-ጉባኤው ሌሎች ሥራዎች በዝርዝር የሚወጣ ሌላ ሕግ ይወሰናል፡፡
አንቀጽ 54
የምክትል አፈ–ጉባኤው ስልጣንና ተግባር
- በአፈ -ጉባኤ ተለይቶ የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
- አፈ-ጉባኤው በማይኖርበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፡፡
አንቀጽ 55
የም/ቤቱ አባላት መብትና ግዴታ
- ማንኛውም የም/ቤቱ አባል በም/ቤቱ በሚሰጠው ድምጽ ወይም አስተያየት ምክንያት አይከሰስም አስተዳደራዊ እርምጃ አይወሰድበትም፡፡
- ማንኛውም የም/ቤቱ አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፈንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ም/ቤቱ ፈቃድ አይያዝም በወንጀልም አይከሰስም፡፡
- ማንኛውም የም/ቤቱ አባል የመረጠው ሕዝብ አመኔታ በጣበት ጊዜ ከም/ቤት አባልነት ይወገዳል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይዋሰናል፡፡
አንቀጽ 56
የም/ቤቱ የስብሰባ ጊዜና የሥራ ዘመን
- ም/ቤቱ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፡፡
- የም/ቤቱ አባላት የሥራ ዘመን ለአምስት አመት ነወ፡፡ የስራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፈት አዲስ ምርጫ ተካሄዶ ይጠናቀቃል፡፡ የቀድሞው ም/ቤት የሥራ ዘመን በተጠናቀቀ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አዲሱ ም/ቤት ሥራውን ይጀምራል፡፡
- የም/ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በማይኖርበት ወቀት አፈ-ጉባኤው አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይም ከምክር ቤት አባላት መካከል ከ1/3ኛ በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠሩ ከጠየቁ አፈ-ጉባኤው ስብሰባ እንዲጠሩ ከጠየቁ አፈ-ጉባኤው ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት፡፡
- የም/ቤቱ ስብሰባ በግልጽ ይካሄዳል፡፡ ሆኖም ስብሰባው በዝግ እንዲካናድ በአባላቱ ወይም በክልሉ መስተዳደር ም/ቤት ከተጠየቀና ከም/ቤት አባላት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ጥያቄውን ከደገፉት ዝግ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡
አንቀጽ 57
የውሳኔ አሰጣጥና የአሰራር ሥነ–ሥርዓቶች
- ከም/ቤት አባላት መካከል ከ2/3ኛ የሚሆኑት ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ውሳኔ የሚተለለፈው በም/ቤቱ ስብሰባ ላይ በተገኙት አባላት አብላጫ ድምጽ ይሆናል።
- ምክር ቤቱ አሰራሩንና የሕግ አወጣጥ ሂደቱን አስመልክቶ ዝርዝር ሕጎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡
ክፍል ሁለት
የጉባኤዎች ስልጣንና ተግባር
አንቀጽ 58
የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ ስልጣንና ተግባር
የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ በክልል ም/ቤት ከሚኖረው ስልጣንና ተግባር በተጨማሪ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር በተጨማሪ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡
- ማንኛውም የኢኮኖሚ ልማትና የማህበራዊ ልማት ፖሊሲ ስትራቴጁ በተመለከተ ረቂቅ ሕግ ያመነጫል፣ ለክልሊ ም/ቤት አቅርቦ ይፀድቃል፡፡
- የግብርና ታክስ አዋጆችን ያመነጫል፣ ለክልሊ ም/ቤት በማቅረብ ያፀድቃል፡፡
- የክልሉን በጀት ገምግሞ ለክልሊ ም/ቤት ያቀርባል፤
- በክልሉ የም/ቤት አባላት መካከል አፈ-ጉባፌነት አንድ አባል ይጠቁማል፡፡
- የጉባኤውን ስብሰባ የሚመሩ አፈ-ጉባኤ፣ምክትል ጉባኤና
- የጉባኤው ቃለ ጉባኤ የሚይዝ አንድ ፀሐፊ ይመርጣል፡፡
- የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን በዚህ ህገ መንግስት አንቀጽ 39 መሰረት ተግባራዊ ያደርጋል።