BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

የተሻሻለው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ህገ መንግስት (1995)

 

አንቀጽ 48

ስለ ክልሉ ምክር ቤት አባላት

  1. የክልሉ ምክር ቤት አባላት ነፃ፤ ቀጥተኛ ትክክለኛ በሆነና ድምጽ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ ይመረጣሉ፡፡
  2. የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ወስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪወች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፈ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡ የምክር ቤቱ አባለት ቁጥር የሕዝብ ብዛትን መሠረት ያደረገ ይሆናል፡፡ የማኦና የኮሞ ብሄረሰቦች ውክልና በልዩ ሁኔታ ይታያል፡፡ የጠቅላላ ምክር ቤት አባላት ቁጥር ከአንድ መቶ አይበልጥም የተለየ ውክልና እንደሚያስፈልጋቸው የታመነባቸው ሕዝቦች በምርጫ ምክር ቤቱ ውስጥ ይወከላሉ፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
  3. የምክር ቤት አባላት የመላው ክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ናቸው፡፡ ተገዥነታቸውም፣

ሀ/ ለሕገ-መንግስቱ

ለ/ ለህዝቡና

ሐ/ ለራሳቸው ህሊና ብቻ ይሆናል፡፡

  1. ማንኛውም የክልል ምክር ቤቱ አባል በምክር ቤቱ ስብሰባ በሚሰጠው ድምጽ ወይም አስተያየት ምክንያት አይከሰስም፣ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወስድበትም፡፡
  2. ማንኛውም የክልሉ ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፡፡ በወንጀል አይከሰስም፡፡
  3. ማንኛም የክልሉ ምክር ቤት አባል የመረጠው ህዝብ አመኔታ ባጣበት ጊዜ በህግ መሠረት ከምክር ቤት አባልነት ይወገዳል፡፡
  4. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቅጽ 6 ድንግጌ እንደአግባብነቱ በየደረጃው በሚኙ ምክር ቤቶች ተፈፃሚነት ይኖረዋል፤

አንቀጽ 49

የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር

  1. የክልሉ ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግስት መሠት የክልሉ ሕግ አውጭ አካል ነው፡፡
  2. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪበፑብሊ ሕገ-መንግስት ድንጋጌ እንደጠበቀ ሆኖ የክልሉ ምክር ቤት በክልሉ የውስጥ ጉዳዮች ላይ የበላይ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት ነው፡፡
  3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች ሥር የሰፈረው አጠቃላይ ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ በተለይ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡
  4. በዚህ ሕገ- መንግስት መሠረት የፌደራሉን ሕገ-መንግስትና ሌሎች ሕጎችን የማይፃረሩ ልዩ ልዩ ሕጎችን ያወጣል፡፡

3.2 የሕዝቡን ብዛት፣ የክልሉን ስፋትና ማህበራዊና -ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳዳር እርከኖች ወይም የራስ በራስ አስተዳደራዊ አከባቢዎችን በሕግ ያቋቁማል፡፡

3.3 የፌደራል መንግስት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ከአጐራባች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር የሚደረጉ ስምምነት ያፀድቃል፡፡

3.4 የራሱን አፈ-ጉባኤ ይመርጣል፣ለምክር ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን ይሰይማል፡፡

3.5 ከምክር ቤቱ አባለላት መካከል ርዕሰ መስተዳድሩን በምርጫ ይሰይማል፣ በርዕሰ መስተዳድሩና አቅራቢነት የክልሉን ካቢኔ ምክር ቤት አባላት ሹመት ያፀድቃል፤

3.6 በርዕሰ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ኘሬዚዳንት፤ ም/ኘሬዚዳንት፤ ዋና  ኦዲተሩንና ምክትል ዋና ኦዲተርን ይሾማል፤

3.7 የክልሉን የክልሉን ጠቅላይ ፤ ከፍተኛ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ያቋቁማል፤ ዳኞችን  ይሾማል፤

 3.8 የኦዲትና የቁጥጥር አካል ያቋቁማል፡፡

3.9 የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ መመሪያወችን ያወጣል፤ የፀጥተና የፖሊስ ኃይሉን ያቋቁማል፤

3.10 የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኘሮግራሞች ያፀድቃል፤

3.11 የክልሉን የገቢ ምንጮች የሚመለከቱ ሕጐችን ያወጣል፤ የክልሉን በጀት ለብሄረሰብ ምክርቤቶች ለአስተዳደራዊ እርከኖችና ወረዳዎች በቀመር ይመድባል፤ መርምሮ ያፀድቃል፤

3.12 ለማህበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት፤ ለኢኮኖሚያዊ ልማት መፋጠንና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን ያቋቁማል፤

3.13 ለክልሉ መንግስት በተከለለው የገቢ ምንጭ ግብርና ታክስ ይጥላል፤

3.14 የክልል መስተዳድሩን የሠራተኛ አስተዳደርና  የስራ ሁኔታዎችና በተመለከተ ሕግ ያወጣል፤

3.15 በዚህ ሕገ መንግስት አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ /2.17/ ሥር ለክልሉ መንግስት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጣል፤

3.16 የሀገሪቱንና የክልሉን ሕግጋተ መንግስት አዋጆችን ሌሎች ሕጐችን በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር የማስፈፀሚያ ደንቦችን ያወጣል፤

3.17 የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች የክልሉን መንግስት ባለስልጣናት ለጥያቄ ይጠራል፤የአስፈፃሚውን አካል አሠራር ይመረምራል፤

አንቀጽ 50

የፖለቲካ ሥልጣን

በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ድርጅቶች የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ያደራጃል ወይም ያደራጃሉ፤ ይመራል ወይም የመራሉ፤

  1. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቅጽ 1 ድንጋጌ እነደየአግባብነቱ ለብሔረሰብ ምክር ቤት እና ለቀበሌ አስተዳደር ምክር ቤት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አንቅጽ 51

ስለ ክልሉ ምክር ቤት /ቤት

  1. የክልሉ ምክር ቤት የራሱ ጽ/ቤት ይኖረዋል፤
  2. የጽ/ቤቱ ሥልጣንና ተግባር በህግ ይወስናል

አንቀጽ 52

ስለ ምክር ቤቱ አፈጉባኤ አሰያየምና የስራ ዘመን

  1. የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በዚህ ሕገ መንግስት አንቅጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 3/3.4/5 መሠረት ከም/ቤቱ አባላት መካከል በምርጫ የሚሰየም ሆኖ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ነወ፡፡
  2. የአፈ-ጉባኤው የሥራ ዘመን የክልሉ ምክር ቤት የሥራ ዘመን ይሆናል፡፡

አንቀጽ 53

የአፈጉባኤው ሥልጣንና ተግባር

የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ በዚህ ሕገ መንግስት መሠረት የሚከተለሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል።

  1. የምክር ቤቱን መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎች ይጠራል፤ይመራል፤
  2. መክርቤቱን በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወከላል፤
  3. የምክር ቤቱን ጽ/ቤት ያደራጃል፤ ጠቅላላ የአስተዳደር ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፤
  4. ምክር ቤቱ በአባሎቹ ላይ እንዲወሰድ የወሰነውን የዲሲፒሊን እርምጃ ይፈድማል፤
  5. የምክር ቤቱን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ያስተባብራል፤

አንቀጽ 54

የምክትል አፈጉባዔው ሥልጣንና ተግባር

ምክትል አፈ-ጉባዔው ተጠሪነቱ ለአፈ-ጉባዔውና ለክልሉ ምክር ቤት ሆኖ፡-

  1. በአፈ-ጉባዔው ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
  2. አፈ-ጉባኤው በማይኖርበት ወይም ሥራውን ለማከናወን በማይቻልበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፤

አንቀጽ 55

የምክር ቤቱ የስብሰባ ጊዜና የሥራ ዘመን

  1. የክልሉ ም/ቤት ቢያነስ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፤
  2. ከምክር ቤቱ አባላት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡ የምክር ቤቱ ውሳኔ በስብሰባው ላይ በተገኙት የምክር ቤት አባላት የአብላጫ ድምጽ ይተላለፋል፡፡
  3. የክልሉ ምክር ቤት አባላት የሚመረጡ ለአምስት አመታት ነው፡፡ የሥራ ዘመኑ ከብቃቱ ከንድ ወር በፈት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ይጠናቀቃል፤ የቀድሞው የምክር ቤት የሥራ ዘመን በተጠናቀቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት ሥራውን ይጀምራል፤
  4. ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በማይደረግበት ወቅት አፈ-ጉባዔው አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይም ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ከንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቁ አፈ-ጉባኤውቨ የምክር ቤቱን ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት፡፡
  5. የክልሉ ምክር ቤቱ ስብሰባ በግልጽ ይካሄዳል፤ ሆኖም ስብሰባው በዝግ እንዲካሄድ በምክር ቤቱ አባላት ወይም ወይም በክልሉ የአስፈፃሚ አካል ከተጠየቀና ከምክር ቤቱ አባለት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ጥያቄውን ከደገፉት ዝግ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡

አንቀጽ 56

የምክር ቤቱ ውሣኔዎችና ውስጣዊ የአሠራር ሥነ ሥርዓቶች

  1. በዚህ ህገ መንግስት ውስጥ ተገልጾ በተለይ ካልተደነገገ በስተቀር ማናቸውም ውሳኔዎች የሚላለፉት በምክር ቤቱ አባላት የአብላጫ ድምጽ ይሆናል፡፡
  2. ምክር ቤቱ ውስጣዊ አሠራሩንና የሕግ አወጣጡን ሂደት አስመልክቶ ዝርዝር ደንቦችን ሊያወጣና በስራ ላይ ሊያውል ይችላል፡፡

አንቀጽ 58

የክልል መስተዳዳር ምክር ቤት

  1. የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች በሕግ በሚወሰነው መሠት ሌሎች አባላት የሚኙበት አካል ነው፡፡
  2. የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሰብሳቢ ርዕሰ መስተዳድሩ ነው
  3. የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለርዕሰ መስተዳድሩ ነው፡፡
  4. የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በሚወስነው ውሳኔ ለክልሉ ምክር በት ተጠሪ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 59

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር

የፌደራሉ ሕገ መንግስት ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ከዚህ በታች የተመለከቱት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

  1. በክልሉ ምክር ቤት በፌደራሉ መንግስት የወጡ ሕጐችና የተላለፉ ውሳኔዎች በክልሉ ውስጥ በስራ መተርጐማቸውን ያረጋግጣል፤ መመሪያዎችን ይወጣል፤
  2. የክልል መስተዳድሩ አስፈፃሚ አካላት የሌሎች ተቋማት አደረጃዳት ይወስናል፤ ሥራቸውን ይከተተላል፤ ይመራል፤
  3. በዚህ ሕገ መንግስት አንቅጽ 45 ንዑስ አንቀጽ 1 እና አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ2 ድንጋጌዎች ሥር ለክልሉ ም/ቤት የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉ ወስጥ ከሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሚቀርቡ የሽግሽግ ጥያቄዎችን አጣርቶ ይወስናል፤
  4. የክልሉን ዓመታዊ በጀት ያዘጋጃል ለክልሉ ምክር ቤት ያቀርባል ፤ ሲፀድቅም በተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
  5. የክልሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎች ይነድፋል፤ የሕግ ረቂቆችን ለክልሉ ምክርቤት አቅርቦ ያስፀድቃል፤ የተወሰነውምንም ያስፈጽማል፤
  6. በክልሉ ውስጥ ሕግና ሥርዓት መከበሩን ያረጋግጣል፤ በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል፡፡
  7. የክልሉ ምክር ቤት በሚሰጠው ሥልጣን መሠረት ደንቦችን ያወጣል፤
  8. በዚህ ሕገ መንግስት አንቀጽ 61 ንዑስ አንቀጽ 3 /ሸ/ መሠረት የሚቀርቡለትን ኃላፊዎች ይሾማል።
  9. በዚህ ሕገ መንግስት አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 3 /3.15/ ሥር ለክልሉ ምክር ቤት አስቀድሞ የተሰጠው ሥልጣን እንተደጠበቀ ሆኖ የጤና ችግርና ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋ በክልሉ ውስጥ በሚደርስበት ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ ድንጋጌ አውጥቶ በስራ ላይ ያውላል፡፡
  10. የክልሉ ቅርሳቅርስና የተፈጥሮ ሀብት አስፈላጊው እንክብካቤና ጥበቃ የተደረገለት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
  11. በክልሉ ምክር ቤት የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

አንቀጽ 60

የርዕሰ መስተዳድሩ አሰያየምን የስራ ዘመን

  1. ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ምክር ቤት ውስጥ አብላጫ መቀመጫ ባገኘው የፖለቲካ ድርጅት ወይም ድርጅቶች አቅራቢነት ከክልሉ ምክር ቤት አባላት መካከል በምርጫ ይሰየማል፡፡
  2. በዚህ ሕገ መንግስት በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር የርዕሰ መስተዳድሩ የስራ ዘመን የክልሉ ምክር ቤቱ የስራ ዘመን ነው፡፡

አንቀጽ 75

የብሔረሰብ ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር

  1. እያንዳንዱ የብሔረሰብ ምክር ቤት ለክልል ምክር ቤት አባልነት የተመረጡትን ጨምሮ በውስጡ ከታቀፉት የወረዳ ም/ቤቶች በልዩ ሁኔታ የሚመረጡ አባላት ያሉበት ሆኖ ይቋቋማል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
  2. በኢትዮጽያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሉክ ሕገ-መንግስት ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮችና ለፌደሬሽን ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግስት ደግሞ ለክልሉ ምክር ቤት የተሰጣቸው ሥልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ የብሔረሰብ ምክር ቤቶች የየብሔረሰባቸው የበላይ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸው፡፡
  3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ሥር የሠፈረው አጠቃላይ ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ እያንዳንዱ ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ሲሆን የሚከተሉት ልዩ ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

ሀ/  የሚጠቀምበትን የስራ ቋንቋ

ለ/ ብሔረሰቡ በቋንቋው ለመናገርና ለመፃፍ፤ ቋንቋውን ለማሳደግ ፤ ለመጠበቅ፤ ለመግለጽ፤ ለማዳበርና ለማስፋፋት፤ እንዲሁም ታሪኩን ለመንከባከብ ያለውን መብት ማስጠበቅ፤

ሐ/ በዚህ ሕገ-መንግስት ውስጥ ለክልሉ ምክር ቤት የተሰጠው የሕግ አውጭነት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በተደራጀብት አከባቢ ከክልል አቀፍ ሕግጋት፤ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በማይፃረር ሁኔታ የራሱን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያዎች አውጥቶ በስራ ላይ ማዋል፤

መ/ የክልሉ ምክር ቤት ያፀደቀውን  ዕቅድና በጀት መሠርት በማድረግ የአከባቢውን ዕቅድና በጀት መርምሮ ማጽደቅ፤

ሠ/ የብሔረሰብ ምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ምክትል አፈ-ጉባኤውንና ዋና አስተዳዳሪውን መርጦ ይሰይማል፤

ረ/ በዋና አስተዳዳሪው የሚቀርቡለት የብሄረሰብ አስተዳደሩን ምክትል አስተዳዳሪና ሌሎች የአስተዳደር ምክር ቤት አባላት ሹመት መርምሮ ያፀድቃለ፤

ሰ/ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶች ዳኞች ሹመት ላይ

 የበኩሉን አስተያየት ለክልሉ ምክር ቤት ይሰጣል፤

ሸ/ የብሔረሰብ አስተዳደሩን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደሩን ባለስልጣናት ለጥያቄ ይጠራል አሠራራቸዉንም ይመረምራል፡፡

አንቀጽ 76

ስለብሔረሰብ ምክር ቤት አመራር

  1. የብሔረሰብ ምክር ቤት የራሱ ጽ/ቤት ኖሮት ከምክር ቤቱ አባላት መከካል በሚመረጡ የራሱ አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባኤ ይመራል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
  2. አፈ-ጉባኤውንና ምክትል አፈ-ጉባኤውን ዝርዝር ሥልጣንና ኃላፊነቶች አስመልክቶ በዚህ ሕገ-መንግስት ለክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባኤ የተፃፉት ድንጋጌዎች እንደአግባብነቱ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡
  3. ምክር ቤቱ ለስራው እንደአስፈላጊነቱ ሪሱን በልዩ ልዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች ያደራጃል፤

አንቀጽ 77

የብሔረሰብ ምክር ቤት የስራ ዘመንና የስብሰባ ጊዜ

  1. የብሔረሰብ ምክር ቤት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ይሆናል፡፡ የስራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሄዶ ይጠናቀቃል፡፡ የቀደሞው ምክር ቤት የስራ ዘመን በተጠናቀቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አዲሱ ምክር ቤት ሥራውን ይጀምራል፡፡
  2. የብሔረሰብ ምክር ቤት ቢያንስ በዓመት ሶስት ጊዜ ይሰበስባል፡፡
  3. ከምክር ቤቱ አባላት ውስጥ ከግማሽ በላይ ከተገኙ የስብሰባው ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡ የምክር ቤቱ ውሳኔ በስብሰባው ላይ በተገኙት የምክር ቤቱ አባላት የአብላጫ ድምጽ ይተላለፋል፡፡
  4. የብሔረሰብ ምክር ቤት ስብሰባ በግልጽ ይካሄዳል፡፡ ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በሚያደርግበት ወቅት አፈ-ጉባፌው አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ ወይም ከምክር ቤቱ አባላት መካከል አንድ ሶስተኛው የሚሆኑት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቀ አፈ-ጉባኤው ምክር ቤትን ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ 78

የብሔረሰብ አስተዳዳር ምክር ቤት

  1. የብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ የሕግ አስፈፃሚ አካል የብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱም ለሚመለከተው ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪና ለብሔረሰብ ምክር ቤት ነው፡፡
  2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ሥር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የብሔረሰብ አስተዳዳር ምክር ቤት ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ለርዕሰ መስተዳድሩ ተጨማሪ ተጠሪነት ይኖርበታል፡፡
  3. የበሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ፤ ምክትል አስተዳዳሪና በአስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ አስፈፃሚ መምሪያ ኃላፊዎች የሚካተቱበት አካል ሆኖ ይቋቋማል፡፡

አንቀጽ 79

የብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት የማከተሉትን ሥልጣንና ተግባር

  1. የብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

ሀ/ የብሔረሰብ ም/ቤቱ በክልሉ ምክር ቤትና በፌደራል መንግስት አካለት የወጡ ሕጐችና የተሰጡ ውሳኔዎች በአስተዳደሩ ውስጥ በስራ መተርጐማቸውን ያረጋግጣል፤

ለ/ የአስተዳደር ምክር ቤቱ አባላት የሆኑ መመሪያዎችና ሌሎች አስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት ይወስናል፤ ሥራቸውን ይከታተላል፤ በበላይነት ይመራል፤

ሐ/ የአስተዳደሩን ዓመታዊ በጀት ረቂቅ ያዘጋጃል፤ ለብሔረሰብ ምክር ቤቱ ያቀርባል፤ ሲፀድቅም በተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፤

መ/ የአስተዳደሩ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በዝርዝር ይነድፋል፡፡ በብሔረሰብ ምክር ቤቱ ያፀድቃል፤ የተወሰነውንም ያስፈጽማል፤

 ሠ /በብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ ሕግና ሥርዓት መከበሩንና የሕዝቡ ሠላምና ደህንነት መጠበቁን ያረጋግጣል፤

ረ/ በብሔረሰብ ምክር ቤቱና በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል።

  1. የብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት በመንግስት ተግባራቸው በጋራ ለሚሰጡት ውሳኔና ለሚፈጽሙት ተግባር የጋራ ኃላፊነት አለባቸው፡፡