BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ በወርኃ መጋቢት የተለያዩ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን አከናውኗል። ከእነዚኽ ዋንኛ ኃላፊነቶቹ መካከልም፣ ሕግጋትን ማጽደቅ፣ የሥራ አሥፈፃሚ ተቋማት ሪፖርቶችን ማድመጥ፣ ፓርላመንታዊ ዲፕሎማሲዎችን መከወን እና የመስክ ጉብኝቶችን ማድረግ የወሩ የምክር ቤቱ አበይት ክንውኖች ነበሩ። ከዚያ ባለፈ ከሐምሌ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ከሚያካሂዱት የውክልና ሥራ በተጨማሪ፣ ከየካቲት የለጠቀውን የውክልና ሥራቸውን አከናውነዋል። ከዚኽ አኳያም፣ በዚኹ ወርኃ መጋቢት በዛ ያሉ እንደራሴዎቻቸውን ወደ ተመረጡባቸው የምርጫ ክልሎች በመላክ፣ ዜጎች ያሳስቡናል ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ የመራጭ-ተመራጭ መድረኮችን አካሂደዋል። ይኽች የእንደራሴ ዐሥራ ዐራተኛ ዕትምም፣ እኒኽን ጉዳዮች በመልክ በመልካቸው አጠናቅራ እና ለወሩም እንዲሆን ኹለት የብሪጅ ዳሰሳዊ ምልከታዎችን አካታ እንዲኽ ተጠናቅራለች።