BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

  1. Home
  2. /
  3. Amharic Archive
  4. /
  5. ወርኃዊ ጥንቅር፣ ቁ.005 ሐምሌ 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በእረፍት እና የሥራ ጊዜ ማሻሻያ ዐዋጅ ቁጥር 263/1994 ዓ.ም. መሰረት፣ የእንደራሴዎቹ የእረፍት ጊዜ በየዓመቱ ከየካቲት 1 እስከ 30 እና ከሐምሌ 1 እስከ መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ዋዜማ ድረስ መሆኑ ተደንግጓል። ያም ሆኖ፣ ምክር ቤቱ ወደ እረፍትም ሳይገባ በወርኃ ሐምሌ የተለያዩ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን ከውኗል። ከእነዚኽ ዋንኛ ኃላፊነቶቹ መካከልም፣ ሕግጋት ማውጣት፣ የሥራ አሥፈፃሚ ተቋማት ሪፖርቶችን ማድመጥ፣ ፓርላመንታዊ ዲፕሎማሲ፣ የፌደራል ተቋማትን መጎብኘት እና የመራጭ ተመራጭ ውይይቶችን ማድረግ የወሩ የምክር ቤቱ አበይት ክንውኖች ነበሩ። ከዚኽ በተጨማሪም፣ የእንደራሴዎቹ ምክር ቤት ይኽን መሰሎቹን ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን በተሻለ መልኩ ይከውን ዘንድ አንድ ዓመታዊ ጉባኤም አካሂዷል። ይኽች የብሪጅ አምስተኛ ፣ እነዚኽን የምክር ቤቱን ዕትምም የሐምሌ ክራሞት ጨምሮ፣ በወሩ ያጸደቀውን የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅን ከብሪጅ አጭር ዳሰሳ ጋር አዳብላ እንዲህ ቀርባለች።