BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

መጋቢት

ይኽ ቀዳሚው የመጋቢት ወር የእንደራሴ ዕትም፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ እንደራሴዎች ካከናወኗቸው አበይት ተግባራት መካከል፣ የምክር ቤቱ ተልዕኮዎች የሆኑትን አራት ዋንኛ ጉዳዮችን አካቷል። እነዚህም፣ ሕግ ማውጣት፣ የተመራጭነት ውክልና፣ የአሥፈጻሚ አካላት ቁጥጥር እና የፓርላማ ዲፕሎማሲ ናቸው። ከአሥፈጻሚ አካላት ቁጥጥር ተግባራት ውስጥ የሚካተተው፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትርሚ ዐቢይ አሕመድ፣ የፌዴራል መንግሥቱንት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ፣ እንደራሴዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች መልስ እና ማብራሪያ መስጠታቸው ሲሆን፣ ይኽም የመጋቢት ወር ተጠቃሽ ክንውን ነው። ከዚኽ የርዕሰ-መንግሥቱ ፖለቲካል-ኢኮኖሚ እና የውጪ ጉዳይ ነክ ማብራሪያዎች በተጨማሪም፣ ይኽ የመጀመሪያ ዕትማችን፣ እንደራሴዎች ያጸደቋቸውን ሕግጋት፣ የፈጸሟቸውን የእንደራሴነት የውክልና ተግባራት፣ ያደመጧቸውን የተቋማት ሪፖርቶችና የመስክ ጉብኝቶች፣ እንዲኹም የፈጸሟቸውን የፓርላማ ዲፕሎማሲ ሥራዎችን አሰባስቦ እና በተመረጡት አንኳር ጉዳዮች ላይ የብሪጅን ዳሰሳዊ ምልከታ አካቶ በዚኽ መልክ አቅርቧል።