የጋምቤላ ሕዝቦች በሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕገ መንግስት (1995)
ስለ ክልሉ ምክር ቤት
አንቀጽ 50
ስለ ክልሉ ምክር ቤት አባላት
- የክልሉ ምክር ቤት አባላት ነፃ፤ ቀጥተኛ ትክክለኛ በሆነና ድምጽ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ ይመረጣሉ፡፡
- የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ወስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪወች መካከል አብላጫ ድምጽ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፈ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡ የተለየ ውክልና እንደሚያስፈልጋቸው የታመነባቸው እናሳ በሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን በምርጫ ምክር ቤቱ ውስጥ ይወከላሉ፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
- የምክር ቤት አባላት የመላው ክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ናቸው፡፡ ተገዥነታቸውም፣
ሀ/ ለሕገ-መንግስቱ
ለ/ ለህዝቡና
ሐ/ ለራሳቸው ህሊና ብቻ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም የክልል ምክር ቤቱ አባል በምክር ቤቱ ስብሰባ በሚሰጠው ድምጽ ወይም አስተያየት ምክንያት አይከሰስም፣ አስተዳደራዊ እርምጃም አይወስድበትም፡፡
- ማንኛውም የክልሉ ምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፡፡ በወንጀል አይከሰስም፡፡
- ማንኛም የክልሉ ምክር ቤት አባል የመረጠው ህዝብ አመኔታ ባጣበት ጊዜ በህግ መሠረት ከምክር ቤት አባልነት ይወገዳል፡፡
- የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቅጽ 6 ድንግጌ እንደአግባብነቱ በየደረጃው በሚኙ ምክር ቤቶች ተፈፃሚነት ይኖረዋል፤
አንቀጽ 51
የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር
- የክልሉ ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግስት መሠት የክልሉ ሕግ አውጭ አካል ነው፡፡
- የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪበፑብሊ ሕገ-መንግስት ድንጋጌ እንደጠበቀ ሆኖ የክልሉ ምክር ቤት በክልሉ የውስጥ ጉዳዮች ላይ የበላይ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት ነው፡፡
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች ሥር የሰፈረው አጠቀላይ ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ በተለይ የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡
- በዚህ ሕገ- መንግስት መሠረት የፌደራሉ ሕገ-መንግስትና ሌሎች ሕጎችን የማይፃረሩ ልዩ ልዩ ሕጎችን ያወጣል፡፡
3.2 የሕዝቡን ብዛት፣ የክልሉን ስፋትና ማህበራዊና -ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት በክልሉ ውስጥ በማስገባት በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳዳር እርከኖች ወይም የራስ በራስ አስተዳደራዊ አከባቢዎችን ያቋቁማል፡፡
3.3 የክልሉ ብሄረሰቦችን በመወከል በፌደሬሽን ም/ቤት የሚሳተፉትን በቀጥታ በሕዝብ ባልተመረጡበት ጊዜ ከክልሉ ም/ቤት አባላት መርጦ ይልካል፡፡
3.4 የፌደራል መንግስት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ከአጐራባች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር የሚደረጉ ስምምነት ያፀድቃል፡፡
3.5 የራሱን አፈ-ጉባኤ ይመርጣል፣ለምክር ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን ይሰይማል፡፡
3.6 ከምክር ቤቱ አባለላት መካከል ርዕሰ መስተዳድሩን በምርጫ ይሰይማል፣ በርዕሰ መስተዳድሩና አቅራቢነት የክልሉን ካቢኔ ምክር ቤት አባላት ሹመት ያፀድቃል፤
3.7 በርዕሰ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ኘሬዚዳንት፤ ም/ኘሬዚዳንት፤ ዋና ኦዲተሩንና ምክትል ዋና ኦዲተርን ይሾማል፤
3.8 የክልሉን የክልሉን ጠቅላይ ፤ ከፍተኛ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ያቋቁማል፤ ዳኞችን ይሾማል፤
3.9 የኦዲትና የቁጥጥር አካል ያቋቁማል፡፡
3.10 በሕጐ መሠረት ምህረት ያደርጋል፤ የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ መመሪያወችን ያወጣል፤ የፀጥተና የፖሊስ ኃይሉን ያቋቁማል፤
3.11 የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኘሮግራሞች ያፀድቃል፤
3.12 የክልሉን የገቢ ምንጮች የሚመለከቱ ሕጐችን ያወጣል፤ የክልሉን በጀት መርምሮ ያፀድቃል፤
3.13 ለማህበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት፤ ለኢኮኖሚያዊ ልማት መፋጠንና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን ያቋቁማል፤
3.14 ለክልሉ መንግስት በተከለለው የገቢ ምንጭ ግብርና ታክስ ይጥላል፤
3.15 የክልል መስተዳድሩን የሠራተኛ አስተዳደርና የስራ ሁኔታዎችና በተመለከተ ሕግ ያወጣል፤
3.16 በዚህ ሕገ መንግስት አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 2/7/ ሥር ለክልሉ መንግስት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጣል፤
3.17 የሀገሪቱንና የክልሉን ሕግጋተ መንግስት አዋጆችን ሌሎች ሕጐችን በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር የማስፈፀሚያ ደንቦች ያወጣል፤
3.18 የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች የክልሉን መንግስት አካላት ባለስልጣናት ለጥያቄ ይጠራል፤
3.19 ለብሔረሰብ ዞኖችና ለአስተዳደራዊ እርከኖች የሕዝብ ብዛትን ዋነኛ መመዘኛ ባረገ ቀመር በጀት ይመድባል፡፡
አንቀጽ 52
የፖለቲካ ሥልጣን
- በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ድርጅቶች የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ያደራጃል ወይም ያደራጃሉ፤ ይመራል ወይም የመራሉ፤
- የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቅጽ 1 ድንጋጌ እነደየአግባብነቱ ለብሔረሰብ ዞን፤ ለብሔረሰብ ልዩ ወረዳ፤ ለወረዳ እና ለቀበሌ አስተዳደር ምክር ቤት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
አንቅጽ 53
ስለ ክልሉ ምክር ቤት ጽ/ቤት
- የክልሉ ምክር ቤት የራሱ ጽ/ቤት ይኖረዋል፤
- የጽ/ቤቱ ሥልጣንና ተግባር በህግ ይወስናል
አንቀጽ 54
ስለ ምክር ቤቱ አፈ–ጉባኤ አሰያየምና የስራ ዘመን
- አብላጫ መቀመጫ ባገኙት የፖለቲካ ድርጅት ወይም ድርጅቶች አቅራቢነት የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በዚህ ሕገ መንግስት አንቅጽ 51 ንዑስ አንቀጽ 3/5 መሠረት ከም/ቤቱ አባላት መካከል በምርጫ የሚሰየም ሆኖ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ነወ፡፡
- የአፈ-ጉባኤው የሥራ ዘመን የክልሉ ምክር ቤት የሥራ ዘመን ይሆናል፡፡
- የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች ለብሔረሰብ ዞን፤ ለብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ፤ ለወረዳና ለቀበሌ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች ያገለግላሉ፡፡
አንቀጽ 55
የአፈ –ጉባኤው ሥልጣንና ተግባር
የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ በዚህ ሕገ መንግስት መሠረት የሚከተለሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል።
- የምክር ቤቱን መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎች ይጠራል፤ ይመራል፤
- መክርቤቱን በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወከላል፤
- የምክር ቤቱን ጽ/ቤት ያደራጃል፤ ጠቅላላ የአስተዳደር ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፤
- ምክር ቤቱ በአባሎቹ ላይ እንዲወሰድ የወሰነውን የዲሲፒሊን እርምጃ ይፈድማል፤
- የምክር ቤቱን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ያስተባብራል፤
- በክልሉ ምክር ቤት የሚሰጡትን ሌሎች ተግባሮች ያከናውናል፤
አንቀጽ 56
የምክትል አፈ–ጉባዔው ሥልጣንና ተግባር
ምክትል አፈ-ጉባዔው ተጠሪነቱ ለአፈ-ጉባዔውና ለክልሉ ምክር ቤት ሆኖ፡-
- በአፈ-ጉባዔው ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
- አፈ-ጉባኤው በማይኖርበት ወይም ሥራውን ለማከናወን በማይቻልበት ጊዜ ተክቶ ይሰራል፤
አንቀጽ 57
የምክር ቤቱ የስብሰባ ጊዜና የሥራ ዘመን
- የክልሉ ም/ቤት ቢያነስ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፤
- ከምክር ቤቱ አባላት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
- የክልሉ ምክር ቤት አባላት የሚመረጡ ለአምስት አመታት ነው፡፡ የሥራ ዘመኑ ከብቃቱ ከንድ ወር በፈት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ይጠናቀቃል፤ የቀድሞው የምክር ቤት የሥራ ዘመን በተጠናቀቀ 15 ቀናት ውስጥ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት ሥራውን ይጀምራል፤
- ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በማይደረግበት ወቅት አፈ-ጉባዔው አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይም ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ከንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቁ አፈ-ጉባኤው ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት፡፡
- የክልሉ ምክር ቤቱ ስብሰባ በግልጽ ይካሄዳል፤ ሆኖም ስብሰባው በዝግ እንዲካሄድ በምክር ቤቱ አባላት ወይም ወይም በክልሉ የአስፈፃሚ አካል ከተጠየቀና ከምክር ቤቱ አባለት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ጥያቄውን ከደገፉት ዝግ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡
አንቀጽ 58
የምክር ቤቱ ውሣኔዎችና ውስጣዊ የአሠራር ሥነ ሥርዓቶች
- በዚህ ህገ መንግስት ውስጥ ተገልጾ በተለይ ካልተደነገገ በስተቀር ማናቸውም ውሳኔዎች የሚላለፉት በምክር ቤቱ አባላት የአብላጫ ድምጽ ነው፡፡
- ምክር ቤቱ ውስጣዊ አሠራሩንና የሕግ አወጣጡን ሂደት አስመልክቶ ዝርዝር ደንቦችን ሊያወጣና በስራ ላይ ሊያውል ይችላል፡፡