BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ዝክረ ሕግ ስለ ክልሉ ምክር ቤት

ንቀጽ 49

የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር

  1. የክልሉ ምክር ቤት በዚህ ሕገ መንግስት መሠት የክልሉ ሕግ አውጭ አካል ነው፡፡
  2. የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪበፑብሊ ሕገ-መንግስት ድንጋጌ እንደጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ በብሄራዊ ክልሉ የውስጥ ጉዳዮች ላይ የበላይ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት ነው፡፡
  3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች ሥር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ በተለይ የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡

3.1.  በዚህ ሕገ- መንግስት መሠረት የፌደራሉን ሕገ-መንግስትና ሌሎች ሕጎችን የማይፃረሩ ልዩ  ልዩ ሕጎችን ያወጣል፡፡

3.2. የሕዝቡን ብዛት፣ የክልሉን ስፋትና ማህበራዊና -ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ የአስተዳዳር እርከኖች ወይም የራስ በራስ አስተዳደራዊ አከባቢዎችን ያቋቁማል፡፡

3.3. የፌደራሉ መንግስት ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ከአጐራባች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ጋር የሚደረጉ ስምምነቶችን ያፀድቃል፡፡

 3.4. የራሱን አፈ-ጉባኤ ይመርጣል፣ለምክር ቤቱ ሥራ የሚያስፈልጉትን ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን ይሰይማል፡፡

3.5. ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ርዕሰ መስተዳድሩን ኘሬዚዳንት ይመርጣል፣ የክልሉን መስተዳድር ምክር ቤት አባላት ሹመት ያፀድቃል፤

3.6 በርሰ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉን ጠቅላይ ፍ/ቤት ኘሬዚዳንት ምክትል ኘሬዚዳንት፤ ዋና ኦዲተሩን ምክትል ኦዲተርን ይሾማል፤

3.7 የክልሉን ጠቅላይ ፤ ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የቋቁማል ዳኞችን ይሾማል

 3.8  የኦዲትና የቁጥጥር አካል ያቋቁማል፡፡

3.9  በህጉ መሰረት ምህረት ያደርጋል የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን የፀጥታና የፖሊስ ኃይል ያቋቁማል፤

 3.10. የብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ኘሮገራሞች ያፀድቃል፤

 3.11. የብሔራዊ ክልሉን የገቢ ምንጮች የሚመለከቱ ሕጐችን ያወጣል፤ የክልሉን በጀት ያፀድቃል፤

3.12 ለማህበራዊ አገልግሎት መስፋፋት፤ ለኢኮኖሚያዊ ልማት መፋጠን  አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን ያቋቁማል፤

3.13. ለክልሉ መንግስት በተከለለው የገቢ ምንጭ ግብርና ታክስ ይጥላል፤

3.14 የክልል መስተዳድሩን የሠራተኛ አስተዳደርና  የስራ ሁኔታዎችን በተመለከተ ሕግ ያወጣል፤

3.15 በዚህ ሕገ መንግስት አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ /2/17/    ስር ለክልሉ መንግስት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጣል፤

3.16 የሀገሪቷንና የክልሉን ሕግጋተ መንግስታት፤ አዋጆችና ሌሎች ሕጎችን በክልሉ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር የማስፈፀሚያ ደንቦችን ያወጣል፤

3.17 የክልሉን ኘሬዚዳንትና ሌሎች የክልሉን መንግስት አካላት ባለስልጣናት ለጥያቄ ይጠራል፤ የክልል መስተዳደሩን ምክርቤት አሠራር ይመረምራል፤

አንቀጽ 50

ስለ ክልሉ ምክር ቤት /ቤት

  1. የክልሉ ም/ቤት የራሱ ጽ/ቤት ይኖረዋል፡፡
  2. የጽ/በቱ ሥልጣንና ተግባር በሕግ ይወሰናል፡፡

አንቀጽ 51

ስለምክር ቤቱ አፈጉባዔ

አሰያየምና የስራ ዘመን

  1. የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በዚህ ሕገ-መንግስት አንጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 3/4/ መሠረት ከም/ቤቱ አባላት መካከል በምርጫ የሚሰየም ሆኖ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ነው፡፡
  2. የአፈ ጉባኤው የስራ ዘመን የክልሉ ም/ቤት የስራ ውመን ይሆናል፡፡

አንቀጽ 52

የአፈጉባኤው ሥልጣንና ተግባር

የክልሉ ም/ቤት አፈ-ጉባኤ በዚህ ሕገ-መንግስት መሠረት የሚከተሉት ሥላጠንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

  1. የም/ቤቱን መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎች ይጠራል፤ ይምራል፤
  2. ም/ቤቱን በሶስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወክላል፤
  3. የም/ቤቱን ጽ/ቤት ያደራጃል፤ ጠቅላላ የአስተዳደር ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፤
  4. ም/ቤቱ በአባሎቹ ላይ እንዲወስድ የመሰነውን የዲሲኘሊን እርምጃ ያስፈጽማል
  5. በክልሉ ም/ቤት የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

አንቀጽ 53

የምክትል አፈጉባዔው ስልጣንና ተግባር

 የምክትል አፈ-ጉባኤው ተጠሪነቱ ለአፈጉባኤውና ለክልሉ ም/ቤት ሆኖ፡-

  1. በአፈ-ጉባኤው ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
  2. አፈ-ጉባኤው በማይኖርበት ወይም ሥራውን ለማከናወን በማይችልበት ጊዜ ተክቶ ይሠራል፡፡

አንቅጽ 54

የምክር ቤቱ  የስብሰባ ጌዜና የስራ ዘመን

  1. የክልሉ ምክር ቤት ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፤
  2. ከምክርቤቱ አባላጽ መካከል ከዑለት ሶስተኛው በላይ የሚሆኑት በስብሰባው ላይ ከተገኙ የስብሰባው ምልአተ -ጉባዔ ይሆናል፡፡ የምክር ቤቱ ውሳኔ በስብሰባው ላየ በተገኙ የምክር ቤቱ አባላት የአብላጫ ድምጽ ይተላለፋል
  3. የክልሉ ምክር ቤት አባላት የሚመረጡት ለአምስት ዓመታት ነው፡፡ የስራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሄዶ ይጠናቀቃል፤ የቀድሞው ምክር ቤት  የስራ ዘመን በተጠናቀቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ  አዲሱ ምክር ቤት ሥራውን ይጀምራል፡፡

 

  1. ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በማያደርግበት ወቅት አፈጉባኤው አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይም ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቁ አፈጉባኤው ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት፡፡
  2. የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ በግልጽ ይካሄዳል፤ ሆኖም ስብሰባው በዝግ እንዲካሄድ በአባላቱ ወይም በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ከተጠየቀና ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ጥያቄውን ከደገፉት ዝግ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡

አንቀጽ 55

የምክር ቤቱ ውሳኔዎችና ውስጣዊ የአሠራር ሥነ ሥርዓቶች

  1. በዚህ ሕገ መንግስት ውስጥ ተገልጾ በተለይ ካልተደነገገ በስተቀር ማናቸውም ውሳኔዎች የሚተላለፉት በስብሰባው ላይ በተገኙት የምክር ቤቱ አባላት አብላጫ ድምጽ ይኞል፡፡
  2. ምክምር ቤቱ ውስጣዊ አሠራሩንና የሕግ አወጣጡን ሂደት አስመልክቶ ዝርዝር ደንቦችን ሊያወጣና በስራ ላይሊያውል ይችላል