BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

ንቀጽ 46

ሰለክልሉ ምክር ቤት አባላት

  1. የክልሉ ምክርቤት አባለት ነፃ ቀጥተኛ በሆነና ድምጽ በሚስጥር በሚሰጥበት የምርጫ ሥርዓት በየአምስት አመቱ በህዝብ ይመረጠሉ
  2. የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ ከሌሎች ተወዳዳረዎች መካከል አብላጫ ስምፅ ያገኘ ተወዳዳረ አሽናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡ ዝርዝሩ በህግ ይወሰናል፡፡
  3. የምክር ቤቱ አባላት የመላዉ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ናችዉ፡፡ ተገዥነታቸዉም

ሀ. ለህገ መንግሥቱ፤

ለ. ለመረጣቸዉ ህዝብና

ሐ. ለህሊና ብቻ ይሆናሉ፡፡

  1. ማንኛዉም የምክር ቤቱ አባል በምክር ቤቱ ዉሰጥ በሚሰጠዉ ድምፅ ወይም አሰተያየት ምክንያት አይክሰስም አሰተዳድራዊ እርምጃ አይወሰደበትም፡፡
  2. ማንኛዉመወ የክልል ምክር ቤት አባል ከበድ ወንጀል ሲፈጸም እጅ ክፋንጅ ካልተያዘ በስትቀር ያለምክር ቤት ፊቃድ አይያዘም በወንጀል አያከሰስም፡፡
  3. ማንኛዉም የምክር ቤት አባል የመረጠዉ ህዝብ አመኔታ ባጣባት  ጊዜ በህጉ መሠረት ከምክር ቤት አናላት ይወገዳል፡፡

አንቀፅ 47

የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር

  1. የክልሉ ምክር ቤት በዜህ ህገ መንግስት መሠረት የክልሉ ህግ አዉጪ አካል ነዉ፡፡
  2. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግስት ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ በብሔራዊ ክልሉ የዉስጥ ጉዳዮች ላይ የበላይ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤት ነዉ፡፡
  3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች ስር የሰፈራዉ አጠቃላይ ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤት በተለይ የሚከተሉት ስልጣንና ሃላፈነቶች ይኖሩታል፡፡

ሀ.  በዚህ ህገመንግሥት መሠረት የፌደራሉን ህገመንግስትና ሌሎች ህጐችን የማይጸረሩ ልዩ ልዩ ህጐች ያወጣል፡፡

ለ. የህዝብን ብዛት  የክልሉን ስፍትና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አመት ውስጥ በማስገባት በክልሉ የውስጥ ጉዳዮች ላይ የበላይ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤት ነው፡፡

ሐ. የፌደራሉ መንግስት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ከአጉራባች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ጋር የሚደረጉ ስምምነቶችን ያፀድቃል፡፡

መ. የራሱን አፈጉባኤና ምክትል አፈጉባኤ ይመርጣል ለምክር ቤቱ ሥራ የሚስፈልጉትን ቁሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ይሰይማሉ፡፡

ሠ. ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ርዕሰ መስተዳድሩን በምርጫ ይሰይማል በርዕስ መስተዳድሩን በምርጫ ይሰይማል በርዕስ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉን ምክትል መስተዳድርና የመስተዳድር ምክር ቤት አባላት ሹመት የፀድቃል፡፡

ረ. በርዕስ መስተዳድሩ አቅራቢነት የክልሉን ጠቅላይ ፍ/ቤት ኘሬዚዳንት፣ ምክትል ኘሬዝዳንት፣ ዋና ኦደተሩንና ምክትል ዋና ኦዲተሩን ይሾማል፡፡

ሰ. የክልል ፣ የዞንና የወረዳ የዳኝነት አካላትን ያቋቁማል

ሸ. የኦዲትና የቁጥጥር አካሉን ያቋቁማል፡፡

ቀ. በህጉ መሠረት ምህረት ያደርጋል፡፡

በ. የክልሉን ሠላምና ፀጥታ ለመጠበቅ የሚያስጸልጉ መመሪዎች ያወጣል የፀጥታና የፖሊስ ሃይሉን ያቋቁማል፡፡

ተ. የብሔራዊ ክለሉን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኘሮግራሞች ያፀድቃል፡፡

ቸ. የብሔራዊ ክልሎን የገቢ ምንጮች የሚመለከቱ ህጐች ያወጣል የክልሉን በጀት መርምሮ ያፀድቀል፤

ነ. ለማህበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት ለኢኮኖሚያዊ ልማተ መፋጠንና ለዲሞከራሳዊ ስልጣን ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን የቋቁማል፡፡

ኘ. ለክልሉ መንግስት በተከለለው የገቢ ምንጭ በክልሉ ውስጥ ግብርና ተክስ ይጥላል፡፡

አ. የክልል መስተዳድሩን የሠራተኛ አስተዳዳር የሥራ ሁኔተዎች በተመለከተ ህግ የወጣል፡፡

ከ. በዚህ ህገ መንግስት አንቀጽ 47 ነዑስ 2/ወ/ ሥር ለክልሉ መንግስት በተሰጠው ስልጣን የአስቸኩይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፡፡

ወ. በተለይ በግብርና ልማት ስር የእንስሳት ሀብት ልማት እና በጥታ ጉዳዩ  በሚመለከተው አስፈፃሢ አካል እየተከሃወኑ መሆናቸውን ይከታተላል፡፡

ኀ. የሀገሪቱንና የክልሉን ህግጋተ መንግስታት፤ አዋጀጆችና ሌሎች ህጐችን በክለሉ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር የስፈፀመያ ደንቦችን ያወጣል፡፡

ዐ. የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርግ ሌሎች የክልሉን መንግስት ባለስልጣናት ለጥያቄ ይጠራል፡፡ የአስፈፃሚውን አካል አሠራር ይመረምራል፡፡

አንቀጽ 48

ስለ ክልሉ ምክር ቤት

  1. የክልሉ ምከር ቤት የራሱ ፅሕፈት ቤት ይኖረዋል፡፡
  2. የጽህፈት ቤቱ ሥልጣንና ተግባር በህግ ይወስናል፡፡

አንቀጽ 49

ስለ ምክር ቤት አፈጉባኤ አሰያየምና የሰራ ዘን

  1. የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ በዚህ ህገመንግስት አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 3 /መ/ መሠረት ከምክር ቤቱ አባላት መካከል በምርጫ የሚሰየም ሆኖ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት ነው፡፡
  2. የአፈ ጉባኤው የሥራ ዘመን የክልሉ ምክር ቤት የሥራ ዘመን ይሆናል፡፡

አንቀጽ 50

የአሐፈጉባኤ ስልጠንና ተግባር

የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በዚህ ህገመንግስት መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

  1. የምክር ቤቱን መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባወች ይጠራል ይመራል፡፡
  2. ምክር ቤቱን በሦስተኛ ወገኖች ዘንድ ይወክላል፡፡
  3. የምክር ቤቱን ጽሕፊት ቤት ያደራጃል ጠቅላላ የአስተዳደር ሥራዎችን በበላይንት ይመራል፡፡
  4. ምክር ቤቱ በአባሎች ላይ እንዲወስድ የዲስፒሊን እርምጃ ያስፈጽማል፡፡
  5. በክልሉ ምክር ቤት የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናዉናል፡፡

አንቀፅ 51

የምክትል አፈጉብኤ ሥክጣንና ተግናር

ምክትል አፈጉባኤዉ ተጠረነቱ ለአፈጉባኤዉና ለክልሉ ምክር ቤት ሆኖ፡፡

1.በአፈ ጉባኤውተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፡፡

  1. አፈጉባኤው በማይኖርበት ወይመ ሥራውን ለማከናወን በማይችልበት ጊዜ ተክቶ ይሠራል፡፡

አንቀጽ 52

 የምክር ቤቱ የስብሰባ ጊዜና የሥራ ዘመን

  1. የክልሉ ምክር ቤት ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ሰብሰባ ያደርጎለ፡፡
  2. ከምክት ቤቱ አባላት ውስጥ ከሁለት ሶሶተኛው በላይ የሚሆኑት በስብሰባው ላይ በተገኙ የስብሰባው ምልአተጉባኤ ይሆናል፡፡ የምክር ቤቱ ውሳኔ በስብሰባው ላይ በተገኙ የምክር ቤቱ አባላት የአብላጫ ድምጽ ይተላለፋል፡፡
  3. የክልሉ ምክር ቤት አባላት የሚመረጡት ለአምስት ዓመታት ነው የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሄዶ ይጠናቀቃል፡፡ የቀድሞው ምክር ቤት የሥራ ዘንድ በተጠናቀቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አዲሱ ምክር ቤት ሥራውን ይጀምራል፡፡
  4. ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በማይደርግበት ወቅት አፈጉባኤው አስቸኩይ ስብሰባ ጪጠራ ይችላል የክልሉ ርዕስ መስተዳድር ወይመ ከምክር ቤቱ አባላት መካከል ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ በጠየቁ ጊዜ አፈጉባኤው የምክር ቤቱን ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት፡፡
  5. የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ በግልጽ ይካሄዳል፡፡ ሆኖም ስብሰባው በዝግ እንዲካሄድ በምክር በቱ አባላት ወይመ በክልሉ አስፈፃሚ አካል በተጠየቀና በምክር ቤቱ አባላት መካከል ከግማሽ የሚሆኑት ጥያቄው ከደገፉት ምክር ቤቱ ዘግ ስብሰባ ሊደረና ይችላል፡፡

አንቀጽ 53

የምክር ቤቱ ውሳኔዎችና ውስጣዋ የአሠራር ሥነ ሥርዓቶች

  1. በዚህ ህግ መንግስት ውስጥ ተገልዶ በተለይ ካልተደነገገ በስተቀር ማናቸውም ውሳኔዎች የሚተላለፉት በምክር ቤቱ አባላት የአብላጫ ድምጽ ይሆናል፡፡
  2. ምክር ቤቱ ውሰጣዊ አሠራሩና የህግ አወጣጡን ሂደት አስመልክቶ ዝርዝረ ደንቦችን ሊያወጣና በሥራ ላይ ሊያውል ይችላል፡፡