BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

  1. Home
  2. /
  3. Amharic Archive
  4. /
  5. ወርኃዊ ጥንቅር ቁ.003 ግንቦት 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ በወርኃ ግንቦት የተለያዩ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን ከውኗል። ከእነዚኽ ዋንኛ ኃላፊነቶቹ መካከልም፣ ሕግጋት ማውጣት፣ የሥራ አሥፈፃሚ ተቋማት ሪፖርቶችን ማድመጥ፣ ፓርላመንታዊ ዲፕሎማሲ እና የፌደራል ተቋማትን መጎብኘት የሚጠቀሱት የወሩ የምክር ቤቱ አበይት ክንውኖቹ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም፣ ምክር ቤቱ የራሱን የዘጠኘ ወራት ሥራ አፈፃፀም ጨምሮ፣ ለእንደራሴዎቹም የዐቅም ማጎልበቻ ሥልጠና እንዲሰጥ ሲያደርግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩንም ወደ አዳራሹ ጠርቶ በተለያዩ ውጭ ጉዳይ ተኮር ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠው አድርጓል። ይኽች የብሪጅ ሦሥተኛ ዕትምም፣ እኒህን የምክር ቤቱን የግንቦት ክራሞት ጨምሮ፣ በወሩ ከጸደቁት ሕግጋት መካከል በመረጥነው አንድ ሕግ ላይ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለዴሞክራሲያዊ ፓርላሜንታዊ ስርዓት ግንባታ ስለሚኖረው ሚና አጭር ተቋማዊ ዳሰሳዊ ምልክታችንን አካታ ቀርባለች።