BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

ሚያዚያ

ይኽ የሚያዚያ ወር የእንደራሴ ዕትም፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. እንደራሴዎች ካከናወኗቸው አበይት ተግባራት መካከል፣ የምክር ቤቱ ተልዕኮዎች የሆኑትን ሦስት ዋንኛ ጉዳዮችን አካቷል። እነዚህም፣ ሕግጋት ማውጣት፣ የአሥፈጻሚ አካላት ቁጥጥር እና የፓርላማ ዲፕሎማሲ ናቸው። የዚህ ወር ዕትማችን፣ እንደራሴዎቹ ያጸደቋቸውን ሕግጋት፣ የፈጸሟቸውን የእንደራሴነት የውክልና ተግባራት፣ ያደመጧቸውን የተቋማት ሪፖርቶች እና የከወኗቸውን የመስክ ጉብኝቶች፣ እንዲኹም የፈጸሟቸውን የፓርላማ ዲፕሎማሲ ሥራዎችን አሰባስቦ እና በተመረጡት ኹለት አንኳር ጉዳዮች ላይ የብሪጅን አጭር ዳሰሳዊ ምልከታዎችን አካቶ አቅርቧል።