BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

Amharic PDF

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ በወርኃ ሰኔ የተለያዩ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቶቹን ከውኗል። ከእነዚኽ ዋንኛ ኃላፊነቶቹ መካከልም፣ ሕግጋት ማውጣት፣ የሥራ አሥፈፃሚ ተቋማት ሪፖርቶችን ማድመጥ፣ ፓርላመንታዊ ዲፕሎማሲ፣ የፌደራል ተቋማትን መጎብኘት እና የ2018 ዓ.ም. በጀት ማጽደቁ የሚጠቀሱት የወሩ የምክር ቤቱ አበይት ክንውኖች ናቸው። ከዚኽ በተጨማሪም፣ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ አዳራሹ መተው በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ሰተዋል። ይኽች የብሪጅ አራተኛ ዕትምም፣ እነዚኽን የምክር ቤቱን የሰኔ ክራሞት ጨምሮ፣ በወሩ ያጸደቀውን የቀጣዩን ዓመት በጀት ዝርዝር ነጥቦች ከብሪጅ አጭር ዳሰሳ ጋር አዳብላ እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያዎች መካከል ዋንኞቹን ነጥቦች አጠናክራ እንዲህ ቀርባለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *