- Home
- /
- Amharic Archive
- /
- ወርኃዊ ጥንቅር፣ ቁ.007 ጷግሜ 2017 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከሐምሌ 1 እስከ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት እረፍት ላይ ቢሰነብትም፣ የ2017 ዓ.ም. የመጨረሻዋን ወርኃ ጷግሜን ያሳለፈው ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ የውክልና ሥራዎቹን በማከናወን ነበር። ይኽች የዓመቱ የመጨረሻ የእንደራሴ ዕትምም፣ የእንደራሴዎቹን የጷግሜ የመራጭ-ተመራጭ ክንውኖች፣ በ‘የክልሎቹ አዋቅራ ቀርባለች። ከዚኽ በተጨማሪም፣ እንደራሴዎቹ ዓመቱን እንዴት ከረሙ ስትል፣ እንደራሴዎቹ በዓመቱ ከከወኗቸው አንኳር ጉዳዮች መካከል፣ አንዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር. ዐቢይ አሕመድን ውሎ እና ዋንኞቹ ያለቻቸውን የጸደቁ ሕግጋት አጠቃሎ ይዛለች።