BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

  1. Home
  2. /
  3. Publications
  4. /
  5. ወርኃዊጥንቅር፣ቁ. 009 ጥቅምት 2018 ዓ.ም.

ስድስተኛው የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የመጨረሻው የሆነውን የሥራ ዘመን ኹለተኛ ወሩን ያሳለፈው ተለምዷዊዎቹን ሕገ-መንግሥታዊ ኅላፊነቶቹን በመወጣት ነበር። በቀደመው መስከረም ወር የመክፈቻ ንግግራቸውን ለኹለቱም ምክር ቤቶች ያቀረቡትን የፕሬዝደንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን የ2018 ዓ.ም. የትኩረት አቅጣጫ የውሳኔ ሐሳብ ያጸደቀው ምክር ቤቱ፣ በዚኹ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ አሉኝ ያላቸውን ማብራሪያ የሚሹ ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩም አቅርቦ የመንግሥትን ምላሽ አድምጧል። ምንም እንኳን፣ በዚኹ ወር ላይ ምክር ቤቱ ያጸደቃቸውም ሆኑ ወደ ቋሚ ኮሚቴዎች የመራቸው ሕግጋት ባይኖሩትም፣ ሰፋ ያሉ የአስረጂ መድረኮችን አከናውኗል። ይኽች የወርኃ ጥቅምት የእንደራሴ ዕትምም፣ የጠቅላዩን ዋና ዋና የንግግር ሐሳቦች አጠቃሎን ጨምሮ፣ ምክር ቤቱ በወሩ ያካሄዳቸውን ጉዳዮች ትዳስሳለች፤ ከዚኽ ባለፈም፣ በእንደራሴዎቹ የውክልና ሥራ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ አጭር ዳሰሳዋን ይዛ ቀርባለች።