የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ከኹለት ዓመታት በፊት አንድ ግዙፍ ፖሊሲ አጽድቆ ነበር። ይኽ የሽግግር ፍትሕ የተሰኘው የበዙ ማኅበረ-ፖለቲካዊ እና ተቋማዊ ተጽዕኖዎች ያሉት ፖሊሲ፣ ምንም እንኳን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካጸደቀው ዋለ አደር ቢልም፣ አልፎም የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ-ካርታው ነሐሴ 2016 ዓ.ም. በፍትሕ ሚኒስቴር አማካኝነት ቢዘጋጅም፣ ትግበራው የመዘግየት ኹኔታ ሳይገጥመው አልቀረም። ከዚያ ባለፈም፣ በትግበራው ፍኖተ-ካርታ እንደተቀመጠው፣ የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ሊያጸድቋቸው ይገቡ የነበሩ ፖሊሲውን ማስፈጸሚያ የተለያዩ ዐዋጆች፣ ይኽች ዕትም እስክትዘጋጅ ድረስ ወደ እንደራሴዎቹ ጠረጴዛ አልደረሱም። እነሆ ይኽች ዕትምም፣ እኒኽን ርዕሰ-ጉዳዮች ጨምሮ፣ የእንደራሴዎቹ ምክር ቤት ይኽን ፖሊሲ እና የትግበራ ፍኖተ-ካርታውን አስመልክቶ ይኖሩበታል ተብለው የሚታመኑትን ሕገ-መንግሥታዊ ኅላፊነቶች፣ በፖሊሲው እና በአተገባበሩ ዙሪያ ከተለያዩ ወገኖች በተቆርቋሪነት የሚነሱትን ሒሶች፣ ከዚያ ሻገር ብላም የተቋማችንን ወሳኝ ምክረ-ሐሳቦች አካታ ለማተት ትሞክራለች።
የሽግግር ፍትሕ ሲሉ...
በሰው ልጆች የታሪክ መዛግብት ተሰንደው የምናገኛቸው አያሌ መልካም ነገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ በተቃራኒው ደግሞ የሰው ልጆች ግፍ እና በደል ሲፈጽሙ እና ሲያስተናግዱ ክፍለ-ዘመናትን ተሻግረዋል። በዚኽም በተለይ በበደሉ ገፈት ቀማሾች ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ እና ሀዘን ሰዎችን ለበቀል እያነሳሳ ሌላ ጥፋት ሲያስከትል ማስተዋልም እንግዳ አይደለም። በዚያው ልክ ሰዎች የደረሰባቸውን ግፍ ለማራገፍ ፍትሕን ሲሹ ሰንብተዋል። እምባቸው የሚታበሰው፣ ቁስላቸው የሚሽረው ለደረሰባቸው በደል ካሳ የሚሆን ፍትሕ ሲያገኙ ብቻ እንደሆነም ያምናሉ። በርካታ አገራትም በታሪክ ውስጥ ላጋጠሟቸው ስብራቶች የሽግግር ፍትሕን አማራጭ አድርገው በመጠቀም ለችግሮቻቸው መፍትሔ ያበጃሉ። እ.ኤ.አ. በ1970ዎቹ መጀመሪያ በምሥራቅ አውሮፓ እና በደቡብ አሜሪካ ተግባራዊ በተደረገው የሽግግር ፍትሕ፣ በጦርነት እና በግፍ አገዛዝ የተበደሉ አካላት ፍትሕ እንዲያገኙ የተደረገበት መንገድም ለዚኽ ተጠቃሽ ማሳያ ነው። ከዚህ ጊዜ በኋላ የሽግግር ፍትሕ በተለይ በመደበኛ የሕግ ሥርዓት ብቻ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስቸግሩ ጉዳዮችን ጭምር በተጠያቂነት፣ በይቅርታ፣ በካሳ እና መሰል ቁስል ሻሪ የፍትሕ ማስፈኛ መንገድ ተደርጎ ተወስዷል።
የሽግግር ፍትሕ ማለት በማኅበረሰቡ ውስጥ በስፋት ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ምላሽ የሚሰጥበት አካሔድ መሆኑን ምሁራን ያስረዳሉ። ይኽንን ሂደት ሰላማዊ፣ ኹሉን አካታች እና ተደራሽ ለማድረግ የኹሉም ጥረት እና አጋርነት ቀዳሚ መነሻ ሊሆን እንደሚገባውም ይገልጻሉ። የሽግግር ፍትሕ በአንድ ጊዜ የሚያልቅ ሳይሆን ጊዜ የሚጠይቅ እና ቀላል የማይባሉ ዓመታትን ሊወስድ የሚችልም ነው። ይኽም ለተበዳዮች ፍትሕ በመስጠት፣ ካሳ በመክፈል፣ የወደሙ ንብረቶችን መልሶ በመገንባት እና በመሰል ሂደቶች ሊፈጸም ይችላል። የሽግግር ፍትሕ አገራት ከ‘ርስ በ‘ርስ ጦርነት፣ ከፀብ እና ከመረቀዘ ጥላቻ አዙሪት እንዲወጡ በማድረግ በኩል የማይተካ ሚና እንዳለው የተለያዩ አገራት ተሞክሮዎች ያሳዩናል። ከሰባት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ የፀደቀው የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ፣ የሽግግር ፍትሕ አገራት የተለያዩ መደበኛ እና ባህላዊ ወይም መደበኛ ያልሆኑ የፖሊሲ እርምጃዎችን እና ተቋማዊ አሠራሮችን በመጠቀም የተፈጸሙ ጥሰቶችን፣ ክፍፍሎችን እና አለመመጣጠኖችን ለማስወገድ እና ለደኅንነትም ሆነ ለዴሞክራሲያዊ እና ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጥ ሥርዓት ግንባታ ምቹ ኹኔታዎችን ለመፍጠር የሚደረግ ጠቃሚ እና አስፈላጊ ሂደት እንደሆነ በብዛት ይጠቀሳል።
የሽግግር ፍትሕ በግጭት፣ በጦርነት ወይም ጨቋኝ ሥርዓት በነበረበት ወቅት ለተፈፀመ ጥቃት፣ መጠነ-ሰፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና በደል የተሟላ መፍትሔ መስጠት መቻል ነው። ይኽም በዋናነት ሙሉ ፍትሕ የሚሰጥበትን መንገድ በመዘርጋት ዘላቂ ሰላም፣ እርቅ፣ መረጋጋት እና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት መገንባት የሚቻልበትን ኹኔታ ይመለከታል።
በኢትዮጵያ ተግባራዊ ሊካሄድ የታሰበው የሽግግር ፍትሕ በአራት ዋና ዋና ምክንያቶች አስፈላጊ መሆኑን ፍትሕ ሚኒስቴር መግለጡ ይታወሳል። አንደኛው ኢትዮጵያ የምትገኝበት አገራዊ አውድ ሲሆን፤ በዚኽም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ አለመረጋጋቶች፣ ግጭት እና የ‘ርስ በ‘ርስ ጦርነት ተከስቷል። ይኽም ዜጎችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳት እና ለመፈናቀል ያጋለጠ መሆኑ በገፊ ምክንያትነት ይጠቀሳል። ለ‘ነዚህ ችግሮች ከዚኽ በፊት የተሰጡ ምላሾች ሙሉ አለመሆናቸው የአጥፊዎች እና የተጎጂዎችን ቁጥር ማብዛቱ፣ የበደሎች መደራረብ እና የጥፋቶች ማኅበረሰባዊ ቅርጽ መያዝ በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት እና አካሔድ ፍትሕ መስጠትንም ሆነ ይቅርታ እና እርቅን ማከናወን አላስችል ማለቱ የሽግግር ፍትሕ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓልም ተብሏል።
ኹለተኛው የተሳካ የሽግግር ፍትሕ ለአገረ-መንግሥት ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ፣ ማለትም ባለፉ በደሎች ይቅር ለመባባል፣ እርቅ ለማውረድ፣ ሕዝብ ለማቀራረብ፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ለተፈጸመ በደል እውቅና ለመስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ሦሥተኛው ምክንያት የተሳካ የሽግግር ፍትሕ ሂደት ሳይተገበር የዴሞክራሲ ሽግግርም ሆነ ዘላቂ ሰላም ማስፈን አይቻልም የሚል መሆኑ ተነግሯል። የመጨረሻው በገፊ ምክንያትነት የሚጠቀሰው ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የሽግግር ፍትሕ ወሳኝ መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ በነዚኽ ምክንያቶች የሽግግር ፍትሕን ለማስፈን እየሰራች መሆኑ በበርካቶች ዘንድ በአዎንታዊ መልክ ይጠቀሳል። በተለይ የሽግግር ፍትሕን ተግባራዊ ካደረጉ አገራት ተሞክሮ በመውሰድ ለውጤታማነቱ ከተሰራ በ‘ርግጥም አይነተኛ መፍትሔ ነው። ከአፍሪካ ደቡብ አፍሪካ፣ ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ በቅርቡ ደግሞ ጋምቢያ የሽግግር ፍትሕን ለችግሮቻቸው መፍቻነት ከተጠቀሙ አገራት መካከል መሆናቸውን ማስታወስም ያሻል።
ለመሆኑ ፖሊሲው ምን ይዟል?
የሽግግር ፍትሕ፣ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀሙባቸው አገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። በአገራችንም የሽግግር ፍትሕ አስፈላጊነት ታምኖበት ፖሊሲ ሲዘጋጅ መቆየቱ የሚታወቅ ነው። ይኽ ፖሊሲ ተጠናቆ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀ ሲሆን፣ ፖሊሲው የያዛቸውን ዋንኛ ጉዳዮች መጥቀስ፣ ሀተታችንን ምልዑ ያደርገዋልና፣ ጥቂት ነጥቦችን ከፖሊስው ውስጥ እንፍለቅቅ።
የፖሊሲው መግቢያ፣ በአገራችን በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂ እና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የ‘ርስ በ‘ርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተደረጉ የተለያዩ ሙከራዎችን የሚያብራራ እንዲኹም አኹን ለምን ኹሉን ዓቀፍ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ እንዳስፈለገ የተብራራበት ነው። ፖሊሲው ሦሥት ዋና ዋና ክፍሎችን የያዘ ሲሆን፥ የመጀመሪያው ክፍል ጠቅላላ የፖሊሲ ጉዳዮች የተገጸበት ሲሆን፣ ኹለተኛው ክፍል የፖሊሲ ጉዳዮች እና አቅጣጫዎች የተተነተነበት ነው። የመጨረሻው ክፍል የመንግስት እና የባለድርሻ አካላት ሚና እና የክትትል እና ድጋፍ ሥርዓት ተብራርተውበታል።
በፖሊሲው ክፍል አንድ ሥር የፖሊሲው ዓላማ በግልጽ የተብራራ ሲሆን፤ ይኸውም የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አውድ መሰረት ያደረገ፣ የተቀናጀ እና የተናበበ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላም፣ ዕርቅ፣ የሕግ የበላይነት፣ ፍትሕ እና ዲሞክራሲ የሚረጋገጥበትን መደላድል መፍጠር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል። ፖሊሲው የሚመራባቸው መርሆዎችም በጥልቀት እና በዝርዝር የተብራሩ ሲሆን፤ ዋና ዋና መርሆዎቹም ሰብዓዊ መብት ተኮር የትግበራ ሂደት፣ ከጥቃት ወይም ከጉዳት መጠበቅ፣ አገራዊ ባለቤትነት፣ አውድ ተኮር የአተገባበር ሥርዓት፣ ተጠያቂነት፣ ኹለንተናዊነት፣ አካታችነት እና አሳታፊነት፣ ሥርዓተ-ጾታ ተኮር አተገባበር፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እና አገር በቀል የግጭት አፈታት እሴቶችን ጥቅም ላይ ማዋል ናቸው።
በክፍል ኹለት ሥር የፖሊሲው ጉዳዮች እና አቅጣጫዎች የሚል ዋና ርዕስ ያለው ሆኖ አምስቱ የሽግግር ፍትሕ አምዶችን አስመልክቶ ፖሊሲው ተግባራዊ የሚሆንበት አግባብ የተብራራበት ነው። በዚኹ አግባብ የመጀመሪያው የሽግግር ፍትሕ አምድ የሆነው የወንጀል ተጠያቂነት ሥር ዐራት ዋና ዋና ጉዳዮች የታዩ ሲሆን፤ እነዚኽም ምርመራ እና ክስ የሚወሰንባቸው ወንጀሎች፣ ምርመራ የሚከናወንባቸው እና ክስ የሚመሠረትባቸው አጥፊዎች፣ ወንጀል ምርመራ እና ክስ የሚከናወንበት ተቋማዊ ሥርዓት እና የፍርድ ሂደት የሚከናወንበት ተቋማዊ ሥርዓት ናቸው። ከወንጀል ምርመራ እና ክስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ በሽግግር ፍትሕ ትግበራ ሂደት ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ከባድ ወንጀሎችን መለየት የሚያስችል ግልፅ መለያ መስፈርት በመዘርጋት ጉልህ በሆኑ ወንጀሎች ላይ ትኩረት ያደረገ የክስ ሂደት ይከናወናል ተብሏል። በሽግግር ፍትሕ ትግበራ ሂደት የወንጀል ምርመራ የሚካሔድባቸው እና ክስ የሚመሰረትባቸው አጥፊዎችን በተመለከተ በጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ከፍተኛ ደረጃ የወንጀል ተሳትፎ ያላቸው አጥፊዎች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለ ሲሆን፤ በጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊት የተሳተፉ ነገር ግን ከፍተኛ ደረጃ የወንጀል ተሳትፎ የሌላቸው አጥፊዎችን እንደየአግባብነቱ ሌሎች የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን በመጠቀም ጉዳያቸው የሚታይበት እና መፍትሔ የሚሰጥበት ሥርዓት እንደሚዘረጋም ተብራርቷል።
የክስ ሥራ የሚከናወንበት ተቋማዊ ሥርዓትን በተመለከተ አኹን ካለው የወንጀል ምርመራ እና ዐቃቤ ሕግ ተቋም ውጪ በሆነ፣ ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ ራሱን ችሎ በሚቋቋም እና የሕዝብ አመኔታ በሚኖረው አዲስ የልዩ ዐቃቤ ሕግ ተቋም አማካኝነት የሚከናወን እንደሆነ በፖሊሲው ላይ ተቀምጧል። የፍርድ ሂደት የሚከናወንበት ተቋማዊ ሥርዓትን በተመለከተ በነባሩ ፍርድ ቤት ውስጥ የሽግግር ፍትሕ ጉዳዮችን ብቻ የሚመለከት ልዩ ችሎት እንደሚቋቋምም ተቀምጧል። በሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ኹለተኛው አምድ እውነትን ማፈላለግ፣ ይፋ ማውጣት እና የዕርቅ ተግባር ሲሆን፤ በፖሊሲው እውነት የማፈላለግ፣ ይፋ የማውጣት እና የዕርቅ ሥራ በኹሉም ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ በማተኮር የጥሰቶችን መሠረታዊ ምክንያቶች፣ ተከታታይነት፣ ስልታዊነት፣ መጠነ-ሰፊነት፣ ዓይነት እና የጉዳት መጠን በመለየት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተነግሯል። እውነትን የማፈላለግ፣ ይፋ የማውጣት እና የዕርቅ ተግባራት ከተጽዕኖ እና ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ በሚቋቋም አዲስ የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽን አማካኝነት እንደሚከናወንም በፖሊሲው ላይ በግልጽ ተቀምጧል።
በቅድመ−ኹኔታ ላይ የተመሠረተ ምህረት ሦሥተኛው አምድ ሲሆን ለምህረት ብቁ የሚያደርጉ ቅድመ-ኹኔታዎችን በተመለከተ የሽግግር ፍትሕን በሚያሳልጥ፣ የሕግ የበላይነት እና ተጠያቂነትን በማያስቀር መልኩ በቅድመ−ኹኔታ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ ምህረት በአግባቡ ተዘርዝረው እና ለምህረት ብቁ የሚያደርጉ ኹኔታዎች ተብራርተው በፖሊሲው ውስጥ ተጠቅሰዋል። የምህረት ተግባር የሚከናወንበት ተቋማዊ ሥርዓት ከእውነት ማፈላለግ፡ ማውጣት እና ከዕርቅ ተግባራት ጋር በተሰናሰለ እና ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽኑ ምህረት የመስጠቱን ተግባር በተደራቢነት እንደሚያከነውንም ፖሊሲው አስቀምጧል።
ተግባራዊ የሚደረጉ የማካካሻ ዓይነቶች እና ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮችን በሽግግር ፍትሕ ሂደት ውስጥ አቅምን እና ነባራዊ ኹኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተግባራዊ የሚደረጉ የማካካሻ አይነቶች በዋናነት መልሶ ማቋቋም፣ የማገገሚያ እርምጃዎች፣ ፈውስ፣ የመታሰቢያ እና ማስታወሻ ክንዋኔዎች፣ የጥሰቶችን ሙሉ ሀቅ ማፈላለግ፡ ይፋ ማውጣት እና እውቅና መስጠት እንዲኹም ለተፈጸሙት በደሎች በመንግስት ደረጃ ይፋዊ ይቅርታ መጠየቅ ወዘተ ናቸው። የማካካሻ ሥራን ምህረት ከመስጠት እና ከእውነት ማፈላለግ፣ ይፋ ማውጣት እና የዕርቅ ተግባር ጋር በተሰናሰለ መንገድ የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽኑ የማካካሻ ሥራዎችን የሚያከናውን መሆኑን በፖሊሲው ላይ ተብራርቷል።
ተቋማዊ ማሻሻያን በተመለከተ የተቋማዊ ማሻሻያ ሥራ ትኩረት የሚያደርግባቸው ተቋማት በዋናነት በሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ በተሳተፉ ሰዎች፣ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት በማክበር ወይም በማስከበር ረገድ ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ፣ ወሳኝ ሚና ሊጫወቱ በሚችሉ አገራዊ እና ክልላዊ የፍትሕ፣ የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማት፣ የሚዲያ ተቋማት፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ መብትን ከማስከበር አኳያ ኃላፊነታቸውን ባልተወጡ ተቋማት፣ እና ለሰብዓዊ መብት ጥሰት አስቻይ ኹኔታን በፈጠሩ ሕግጋት፣ ፖሊሲዎች እና አሰራሮች ላይ ቅድሚያ በመስጠት ማሻሻያ እንደሚደረግባቸው በፖሊሲው ላይ በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን፤ የተቋማዊ ማሻሻያ ሥራው ውጤታማ፣ ቀልጣፋ፣ ተቀባይነት እና የሕዝብ አመኔታ እንዲኖረው ለማድረግ ነጻ፣ ገለልተኛ እና ብቃት ባለው ተቋም ማለትም በሕግ እንዲቋቋም በማድረግ ሥራው እንደሚመራ ተብራርቷል።
የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ የሚደረግበትን የጊዜ ወሰን በተመለከተም፣ የሽግግር ፍትሕ የጊዜ ወሰን ለወንጀል ተጠያቂነት ዓላማ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ−መንግሥት ከፀደቀበት ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ ያለው የጊዜ ወሰን ተፈፃሚ የሚደረግ ሲሆን፤ ለእውነት ማፈላለግ፣ ዕርቅ ለማስፈን እና ማካካሻ ሥራዎች ዓላማ ጥሰቶች እና ቅራኔዎችን ከመሰረታቸው በማጥራት ለመመርመር፣ ስብራቶች እንዲሽሩ እና እንዲጠገኑ ለማድረግ እና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት እንዲቻል የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ የተፈፃሚነት ወሰን መረጃ እና ማስረጃ እስከተገኘበት ጊዜ ድረስ ይሆናል በማለትም ፖሊሲ አብራርቷል።
በሽግግር ፍትሕ ትግበራ የክልሎች ሚና በተመለከተ ክልሎች በኹለት ዋና ዋና መንገዶች ሚና የሚኖራቸው ሲሆን፤ የመጀመሪያው በአገር−ዓቀፍ ተቋማት የሚከናውኑ ሥራዎችን በማገዝ ላይ ማተኮር፤ ኹለተኛው ደግሞ በአገራዊ ፖሊሲው አጠቃላይ እሳቤዎች እና እሴቶች ላይ በመመስረት ውስን የሽግግር ፍትሕ ሥራዎችን ራሳቸው በባለቤትነት የሚመሩበትን ሂደት የሚመለከት ነው ተብሏል። በሽግግር ፍትሕ ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶች ሚናን በተመለከተም፣ ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶች ያሉባቸውን ክፍተቶች እንዲስተካከሉ በማድረግ በሚተገበረው የሽግግር ፍትሕ ሂደት ውስጥ ከሌሎች የሽግግር ፍትሕ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እውነትን በማፈላለግ፣ ዕርቅ በማስፈን፣ በማካካሻ እና ምህረት በመስጠት ተግባራት እንዲኹም ማኅበረሰባዊ ሰላምን ለማስፈን በሚደረጉ ሥራዎች ማዕቀፍ ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው በፖሊሲው ላይ ተብራርቷል። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው እና የትግበራ ሂደቱ የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዩች ማለትም ልዩ ትኩረት ለሚሹ እና ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ለሴቶች፣ ለሕጻናት፣ ለወጣቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአረጋውያን እና ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ልዩ ፍላጎት እና ጥቅም ትኩረት በሚሰጥ አግባብ እንደሚከናወን በፖሊሰው ላይ ላይ በጥልቅ ተብራርቷል።
በክፍል ሦሥት ሥር የመንግስት እና የባለድርሻ አካላት ሚና እንዲኹም የክትትል እና ድጋፍ ሥርዓት የተመለከቱ ጉዳዮች የተብራሩበት ሲሆን፤ ዋና ዋና ጉዳዮችም በፖሊሲው መሰረት የሽግግር ፍትሕ ሥራዎችን ተግባራዊ የሚያደርጉ ተቋማት በርከት ያሉ በመሆናቸው፣ እነዚኽ ተቋማት እንዲቋቋሙ ኹኔታዎችን ከማመቻቸት አንስቶ ሥራቸውን ሙሉ ለሙሉ እስኪጀምሩ ድረስ ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማት ተግባር እና ኃላፊነት በዝርዝር የተቀመጠበት ክፍል ነው። ከመንግስት ተቋማት በተጨማሪም የባለድርሻ አካላት ሚና እና የፖሊሲው አፈጻጸም፣ ክትትል እና ድጋፍ ሥርዓትም በሰፊው መብራርቱን ተረድተናል።
ዘገየ ይሆን?
የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ አዝጋሚ ነው የሚል ትችት ሲቀርብበት ይስተዋላል። ለሽግግር ፍትሕ ሂደት ከሕግ ረቂቅ ሰነዶች ውጪ ሌሎች ተግባራት በታቀደላቸው ጊዜ አለመከናወናቸውም አሳሳቢ ነው ሲባል እየተደመጠ ነው። የሽግግር ፍትሕ ሂደትን የሚመራ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁ የሚታወስ ነው። ሆኖም፣ በፍትሕ ሚኒስቴር እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች፣ አጠቃላይ ሂደቱ እየተመራ ያለበት አግባብ ለሕዝብ ግልጽ አለመደረጉም ሲጠቀስ ይስተዋላል። ይኽን የመዘገየት ጉዳይም በስፋት የጠቀሰው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ከጥቂት ወራት በፊት ባወጣው ሪፖርት ነበር። ኮሚሽኑ በሪፖርቱም፣ የሽግግር ፍትሕን የመተግበር የፖለቲካ ቁርጠኝነት በአገሪቱ ያሉ ግጭቶችን የማስቆም ጥረቶችን ሊያካትት ይገባል ብሏል። ለሽግግር ፍትሕ ትግበራ፣ ለግጭቶች እና የጸጥታ ችግሮች ምላሽ ለመስጠት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ውጤታማ አለመሆን አሳሳቢ ተግዳሮት ሆኗል ሲልም አስቀምጧል። ኮሚሽኑ በተለይም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ከተሸጋገረ በኋላ የመቀዛቀዝ አዝማሚያ እያሳየ መሆኑ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ተብሏል።
የመንግስት የታደሰ ቁርጠኝነት ለሽግግር ፍትሕ ጥረቶች በጥንቃቄ የታቀደ እና በቅደም ተከተል የተደራጀ የተቋረጠው ሂደት ዳግም እንዲጀመር መንገድ ሊከፍት ይገባል የሚሉ ድምጾችም ይደመጣሉ። በግንቦት 2017 ዓ.ም.፣ የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር ዋና ዋና የሕግ ማዕቀፎችን አጠናቆ በነበረበት ወቅት፣ መንግሥት ከሽግግር ፍትሕ ይልቅ ለብሔራዊ ምክክር ቅድሚያ ሊሰጥ ይችላል የሚል ግምት ተፈጥሮ ነበር። የምክክር ሂደቱ በቀጣዩ የካቲት ወር እንዲጠናቀቅ ታቅዷል፤ ይኽም ህኦነው፣ በእንደራሴዎቹ ምክር ቤት በጸደቀው የአንድ ዓመት የጊዜ ማራዘሚያ ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ መዘግየቱ፣ በአንዳንድ ታዛቢዎች ዘንድ ሽግግር ፍትሕን እንደ ራሱን የቻለ እና አስፈላጊ የሰላም ግንባታ ሂደት ሳይሆን፣ ከምክክሩ የሚከተል የውሳኔ ሐሳብ አድርገው እንዲመለከቱት ሳያደርግም አልቀረም። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር. ዐቢይ አሕመድ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ለእንደራሴዎቹ ሲናገሩ፣ የኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ በየሽግግር ፍትሕ ጭምር የሚጸና መሆኑን መናገራቸው የዘገየ ለሚለው ድምጽ የተሰጠ ምላሽ ተደርጎ ሊቆጠርም ይችላል። ‘ርሳቸው እንዳሉት፣ የሽግግር ፍትሕ ያለፉ ግፎችን ለመፍታት የታለመ ሲሆን፤ ብሔራዊ ምክክሩ ደግሞ አወዛጋቢ በሆኑ የመንግሥት አሥተዳደር፣ የመንግሥት እና የአገር ግንባታ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለመ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን ጽንሰ ሐሳባዊ ግልጽነት የሰጠ ሲሆን፤ የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ማዕቀፍ ውስጥ ማዕከላዊ ምሰሶ እና ራሱን የቻለ ሂደት መሆኑን አረጋግጧል። ይኽም የሽግግር ፍትሕ የምክክሩ ውጤት ነው የሚሉ ቀደምት ግምቶችን ውድቅ አድርጓል የሚል ዕምነት በተቋማችን ጭምር እንዲያዝ መሆኑን ሳንጠቅስ አናልፍም።
ከሥርዓተ- ጾታ አንጻርስ?
ይኽን የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ሰነድ እና ይተገበራል የተባለውን ፎኖተ-ካርታ አስመልክቶ፣ አንድ ዋንኛ ርዕሰ-ጉዳይን ሳናነሳ ማለፍ አያሻንም፤ ይኸውም፣ ፖሊስውንም ሆነ የትግበራ ሰነዱን ከሥርዓተ-ጾታ አኳያ በጥቂት ነጥቦች ለማንጸር መጣር ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚሰነዘሩ አድሎአዊ ድርጊቶች እና አመለካከቶች ለሴቶች ሕዝባዊ ተሳትፎ ዋና እንቅፋት ከመሆናቸው ባለፈ፣ በዚያም የተነሳ መብቶቻቸው እንደሚጣሱ የበዙ ጥናቶች ያመለክታሉ። እኒኽ ጥናቶች እንደሚጠቅሱት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወንድ የፖለቲካ መሪዎች የሴቶችን የፖለቲካ አመራር በተመለከተ የሴቶች ተሳትፎ እና ውጤታማነት ላይ አሉታዊ አመለካከቶች ሲኖራቸው፤ በሕግ አውጪ እና በአሥፈጻሚነት ቦታ ላይ ያሉ ሴት የፖለቲካ መሪዎች ደግሞ ሴቶች በመንግስት እና በፖለቲካ አመራር ውስጥ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ የበለጠ አዎንታዊ አመለካከቶችን ያነጸባርቃሉ። እነዚኽ አመለካከቶች በተለይም በፖለቲካ እና በማኅበረሰባዊ አመራር ውስጥ የተባዕታይ ፆታ የበላይነትን ከሚያበረታታው ባህል እና ማኅበራዊ ስሪት የመነጩ መሆናቸውም አሌ አይባልም። የኢትዮጵያ ተለምዷዊ አስተሳሰቦች እና ግብሮች ሴቶችን የማኅበረሰብ ወይም የፖለቲካ ተወካይ አድርጎ ከማቅረብ ይልቅ የቤት ውስጥ አገልጋይ ብቻ አድርጎ ወደማየቱ ያዘነብላል። ይኽ የሥርዓተ-ፆታ አድልዎ የተመሰረተው ኅብረተሰቡ ወንዶች የበላይ ውሳኔ ሰጪዎች መሆናቸውን በመቀበሉ ሲሆን፤ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ጥገኛ እና ታዛዥ ሆነው ስለሚታዩ የፖለቲካ ተሳትፏቸው እና ተጽኗቸውም ውስን እንዲሆን አድርጎታል።
በኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚሰነዘሩ አድሎአዊ ድርጊቶች እና አመለካከቶች ለሴቶች ሕዝባዊ ተሳትፎ ዋና እንቅፋት ከመሆናቸው ባለፈ፣ በዚያም የተነሳ መብቶቻቸው እንደሚጣሱ የበዙ ጥናቶች ያመለክታሉ። እኒኽ ጥናቶች እንደሚጠቅሱት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወንድ የፖለቲካ መሪዎች የሴቶችን የፖለቲካ አመራር በተመለከተ የሴቶች ተሳትፎ እና ውጤታማነት ላይ አሉታዊ አመለካከቶች ሲኖራቸው፤ በሕግ አውጪ እና በአሥፈጻሚነት ቦታ ላይ ያሉ ሴት የፖለቲካ መሪዎች ደግሞ ሴቶች በመንግስት እና በፖለቲካ አመራር ውስጥ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ የበለጠ አዎንታዊ አመለካከቶችን ያነጸባርቃሉ። እነዚኽ አመለካከቶች በተለይም በፖለቲካ እና በማኅበረሰባዊ አመራር ውስጥ የተባዕታይ ፆታ የበላይነትን ከሚያበረታታው ባህል እና ማኅበራዊ ስሪት የመነጩ መሆናቸውም አሌ አይባልም። የኢትዮጵያ ተለምዷዊ አስተሳሰቦች እና ግብሮች ሴቶችን የማኅበረሰብ ወይም የፖለቲካ ተወካይ አድርጎ ከማቅረብ ይልቅ የቤት ውስጥ አገልጋይ ብቻ አድርጎ ወደማየቱ ያዘነብላል። ይኽ የሥርዓተ-ፆታ አድልዎ የተመሰረተው ኅብረተሰቡ ወንዶች የበላይ ውሳኔ ሰጪዎች መሆናቸውን በመቀበሉ ሲሆን፤ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ጥገኛ እና ታዛዥ ሆነው ስለሚታዩ የፖለቲካ ተሳትፏቸው እና ተጽኗቸውም ውስን እንዲሆን አድርጎታል።
በሽግግር ፍትሕ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ አመለካከትን ማካተት መሠረታዊ ፍትሓዊነትን እና የሰብዓዊ መብቶች መከበርን እንደማረጋገጥ ይወሰዳል። ማንኛውም የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ሥርዓተ-ፆታን በማካተት፣ በሂደቱም ውስጥ በመጠቀም፣ እንዲኹም ፖሊሲዎችን በመቅረፅ እና በማስፈፀም የሴቶችን እኩል ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያስችላል ተብሎ በብዙዎች ይታመናል። ይኽ አካሔድም ገንቢ ብቻ ሳይሆን ሴቶች በግጭቶች እና በፍትሕ እጦት ጭምርም ይበልጥ ተጎጂ በመሆናቸው እጅጉን አስፈላጊ ያደርገዋል። በመሆኑም ሴቶችን ከሽግግር የፍትሕ ሂደት ማግለል የኹሉንም ተጎጂዎች ፍላጎት በበቂ ኹኔታ ምላሽ መስጠት ካለማስቻሉ ባለፈ፣ ለሰፊው የኅብረተሰብ ለውጥ የበኩሉን አስተዋጽዖ ስለማያደርግ ለስኬታማነቱ እንቅፋት ይሆናል። በኅብረተሰብ ውስጥ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ፍትሓዊ የሥልጣን እና የመብት ክፍፍል አለመኖሩን በመገንዘብ የሥርዓተ-ፆታ ሽግግር ፍትሕ ተገቢ የሆኑትን ዘዴዎች መከተል ይጠይቃልም የሚያስብለው ለዚኹ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ በእያንዳንዱ የፖሊሲ ቀረፃ እና ትግበራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ፣ እንደ ሴቶች ያሉትን ለዘመናት የተገለሉ ወገኖችን ድምጽ፣ ፍላጎት እና መብት በማካተት እውነተኛ ፍትሕ እንዲሰፍን ማድረግ ለሌላ ትውልድ የሚተው ግብር አይመስለንም። የሥርዓተ-ፆታ አመለካከትን ወደ ሽግግር ፍትሕ ማካተት ለፍትሓዊነት እና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ፋይዳ አለው። ለዚኽም በዋንኛ ምክንያትነት መጥቀስ የሚያሻን፣ ሴቶች በፖሊሲ አወጣጥ እና ትግበራ ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባቸውን እኩል ተሳትፎ ከማረጋገጥ ለጥቃት ተጋላጭነታቸውን እና በግጭቶች ወቅት የሚደርስባቸውን ችግር እና የመብት ጥሰቶች እንዲቀንስ ማገዙ ነው፡፡ ይኽ የሥርዓተ-ፆታ አካሔድ ሰላምን ለማስጠበቅ እና ተደጋጋሚ የጥቃት ዑደቶችን ለማስቆም ሁነኛ ዘዴ ነው ተብሎም ይታመናል። እንዳይደመጡ የተደረጉ ድምፆችን እና ፍላጎቶቻቸውን ለማካተት ዘዴዎችን ማበጀት እንዲኹም ገሀድ ለሆነው የኃይል ሚዛን አለመመጣጠን ትኩረት መስጠትን ይጠይቃል። እነዚኽ ሥርዓተ-ፆታን ያማከሉ ጥረቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች ከብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች መገለላቸውን የሚያስተካክሉ ሲሆን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን በደል በማካካስ ለመፍታት ያስችላልም የሚለውንም መጥቀስ ሳያስፈልግ አይቀርም።
በኢትዮጵያ ውስጥ በእያንዳንዱ የፖሊሲ ቀረፃ እና ትግበራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ፣ እንደ ሴቶች ያሉትን ለዘመናት የተገለሉ ወገኖችን ድምጽ፣ ፍላጎት እና መብት በማካተት እውነተኛ ፍትሕ እንዲሰፍን ማድረግ ለሌላ ትውልድ የሚተው ግብር አይመስለንም። የሥርዓተ-ፆታ አመለካከትን ወደ ሽግግር ፍትሕ ማካተት ለፍትሓዊነት እና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ፋይዳ አለው። ለዚኽም በዋንኛ ምክንያትነት መጥቀስ የሚያሻን፣ ሴቶች በፖሊሲ አወጣጥ እና ትግበራ ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባቸውን እኩል ተሳትፎ ከማረጋገጥ ለጥቃት ተጋላጭነታቸውን እና በግጭቶች ወቅት የሚደርስባቸውን ችግር እና የመብት ጥሰቶች እንዲቀንስ ማገዙ ነው፡፡ ይኽ የሥርዓተ-ፆታ አካሔድ ሰላምን ለማስጠበቅ እና ተደጋጋሚ የጥቃት ዑደቶችን ለማስቆም ሁነኛ ዘዴ ነው ተብሎም ይታመናል። እንዳይደመጡ የተደረጉ ድምፆችን እና ፍላጎቶቻቸውን ለማካተት ዘዴዎችን ማበጀት እንዲኹም ገሀድ ለሆነው የኃይል ሚዛን አለመመጣጠን ትኩረት መስጠትን ይጠይቃል። እነዚኽ ሥርዓተ-ፆታን ያማከሉ ጥረቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች ከብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች መገለላቸውን የሚያስተካክሉ ሲሆን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን በደል በማካካስ ለመፍታት ያስችላልም የሚለውንም መጥቀስ ሳያስፈልግ አይቀርም።
ጠንካራ ሥርዓተ-ፆታን ያካተተ የሽግግር የፍትሕ ፖሊሲ በርካታ የመብት ጥሰቶች የሚደርሱባቸውን ሴቶች እና የተገለሉ ቡድኖችን እንደ ልዩ የትኩረት ቡድን እውቅና በመስጠት ሰፋ ያለ አድማስ እንዲኖረው ይጠበቃል። ከሥርዓተ-ፆታ በተጨማሪ ሌሎች ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ኹኔታዋችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ኹሉን ዓቀፍ፣ ተለዋዋጭ፣ ለአዳዲስ አቀራረቦች ዝግጁ እና ተደራሽ መሆን ይኖርበታል። እነዚኽ አካሔዶች በፖሊሲው ውስጥ መካተት እና መዳበር ይኖርባቸዋል። ተግባራዊነቱን ለመከታተል፣ ለመማማር እና እንደ አስፈላጊነቱም ለማሻሻል የሚረዱ መላዎችን በውስጡ ይሸከማል። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ሴቶች በየደረጃው ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን አሰራር በመዘርጋት፣ በፖሊሲ ቀረፃ ሂደት ይደርስባቸው የነበረውን መገለል በመቅረፍ ልዩ ልምዶቻቸውን፣ ፍላጎቶቻቸውን እና አቅማቸውን በማዳበር ላይ ትኩረት ማድረግም ይገባዋል። ይኽ አካሔድ በሥርዓተ-ፆታ ኮታ ብቻ የተገደበ ሳይሆን የሴቶችን ውጤታማ ውክልና ለማረጋገጥ በአቅም ግንባታ፣ በልዩ ሥልጠና እና በባለሙያዎች አመዳደብ ምቹ ኹኔታ መፍጠር ይኖርበታል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ኹሉን ዓቀፍ እና ጾታን ያማከለ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ለመዘርጋት እና ተግባራዊ ለማድረግ ግጭቶች እና ጥቃቶች በሴቶች ላይ የሚኖራቸውን ልዩ ትኩረት መገንዘብ አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን። ይኽም ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ልዩ ተጋላጭነቶች እና የመብት ጥሰቶችን በተለይም ግጭት ወለድ ወሲባዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ልዩ ትኩረት የሚሻ መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል የሚለው በዚኽ ንዑስ ርዕስ ስር ሳንጠቅሰው ማለፍ አንሻም።
ሒሳዊ ትችቶችስ ምን ያነሳሉ?
ይኽን የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አስመልክቶ፣ ከምሁራንም ሆነ ከተለያዩ አገራዊ እና ዓለም ዓቀፍ የመብት ተቆርቋሪ ተቋማት በኩል፣ ሲነሱ የሚስተዋሉ ፖሊሲ እና አተገባበር ተኮር የሙግት ድምጾች መኖራቸውን ተቋማችን ብሪጅ ባደረገችው አጠር ያለ ዳሰሳ ተመልክታለች፤ እናም፣ እነዚህን ሒሳዊ ድጋፍ የሚሰጡት ትችቶችን በተወሰኑ መልኩ መጥቀስ፣ ለቀጣዩ የፖሊስው ትግበራ ኹነኛ ጠቀሜታ አላቸውን በጥቅሉም ቢሆን ብንጠቅሳቸው እና በዋናነትም የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ከታች በመጥይቃዊ መልኩ ጠቅለልን አድርገን ለጠቅስናቸው ነጥቦች ምላሽ የሚሰጡባቸውን አማራጮች ቢሹ ፋይዳቸው ብዙ ነው ብለን እናምናለን። ከዚኽ አኳያም፣ ተቋማችን ብሪጅ ለመሰል ሒሳዊ ትችቶች አግባብነት ያላቸውን ጥናታዊ ምላሾችን በማዘጋጀት አገራዊ ኅላፊነቷን ለመወጣት ዝግጁ እንደሆነችም ማስታወስ ትሻለች፤
የብሪጅ ምክረ ሐሳቦች
ከላይ ከጠቃቀስናቸው ነጥቦች አኳያ፣ ተቋማችን ብሪጅ፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው የታሰበለትን አገራዊ ፋይዳ ያዋልድ ዘንድ ጥቂት ተቋማት ተኮር እና ነባራዊነት ይኖራቸዋል ብላ የምታምንባቸውን ምክር-ሐሳቦች እንደወትሮው ማቅረብ ትሻለች።
አስቀድመን፣ የኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክር ቤት ይኽንኑ የሽግግር ፖሊሲ እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ሊከውናቸው ይገባሉ ያልናቸውን ሕጋዊ እና ተቋማዊ ግብሮች እንጠቅሳለን።
የእንደራሴዎቹ ምክር ቤት ከሽግግር ፍትሕ ሂደት ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ የጠበቀ እና ወሳኝ ነው። ምንም እንኳን ፖሊሲው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቢረቀቅም፣ ምክር ቤቱ ሂደቱን ሕጋዊ እና ተዓማኒ ለማድረግ የሚከተሉት ዐራት ዋና ዋና ሚናዎች ይኖሩታል ተብሎ ይታመናል፤
ሕግጋት እና ሕጋዊ ማዕቀፍ ማበጀት፦
የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከኹለት ዓመታት በፊት ባወጣው የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ፍኖተ-ካርታ፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ወደ ተግባር ለመግባት የተለያዩ አዳዲስ ሕግጋት እንደሚወጡ ይዘርዝራል። ለማስታወስ ያህልም፥
የሚሉትን በዋናነት መጥቀስ ይቻላል። በዚኽ ጉዳይ ላይ ያለን አስተያይትም፣ ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ዐዋጆች በረቂቅ ደረጃ እንደነበሩ ብንረዳም፣ የእነዚኽ ዐዋጆች እስከ ዛሬ አለመውጣት፣ የሽግግር ፍትሑ ዘገየ አልያም ከፋ ካለ አይካሄደም ለሚለው ትችት እጅጉን ሰፊ በር ከፍቷልና፣ የእንደራሴዎቹ ምክር ቤት የቀሩት ወራት ሳይጠናቀቁ ዐዋጆች የሚጸድቁበትን መፍትሔ ቢሻ፣ ከላይ አጠር አድርገን የጠቅስናቸውን ትችቶች ጭምር ይፈታልና ቢታሰብበት የሚል ነው።
ከእነዚኽ እንደራሴዎቹ ተኮር ምክረ-ሐሳቦቻችን ባሻገር፣ ራሱን የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን እና የአተገባበር ፍኖተ-ካርታውን አስመልክቶ ኹለት ነጥቦችን አክለን ማንሳት እንሻለን፤ እነዚኽም፥-