ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ

ማዕከላዊ መንግሥቱ ኃይል የሚጠቀመው በምን ኹኔታ እና ምን ሲገጥመው ነው? የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ጉዳይስ? ኢኮኖሚውስ እንዴት ሰንብቷል? በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 21ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የተገኙት የአገሪቷ ርዕሰመንግሥት፣ ይኽን መሰሎቹን ጥያቄዎች ጨምሮ፣ በዛ ባሉ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ምላሾችን ሰጥተዋል፤ አኹናዊ የመንግሥታቸውን አቋሞችም አስረድተዋል። ኢኮኖሚው እንዴት ሰነበተ?
የምክር ቤቱ የውክልና ሥራ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከሚጠበቁባቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ የውክልና ሥራ ነው። እንደራሴዎቹም ወደ ‘ምርጫ ወረዳዎቻቸው በመሄድ የወከሏቸውን ማወያየት እና ጥያቄዎቻቸውን መስማት፣ በዓመት ኹለት ጊዜ የሚከውኑት ተግባር ነው። ከዚኽ አኳያም፣ የምክር ቤቱ አባላት ይኽንኑ የውክልና ሥራቸውን ከየካቲት ወር በመቀጠል በመጋቢት ወርም ከውነዋል።
የምክር ቤቱ ሕግ የማውጣት ተግባሮች

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኹለት አዋጆችን ያጸደቀ ሲሆን፣ አንድ ረቂቅ አዋጅን ለሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ልኳል፤ ከዚኽ በተጨማሪ፣ ሦሥት የአስረጂ መድረኮችን በረቂቅ ሕጎቹ ላይ አከናውኗል፡፡ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በወርሃ መጋቢት ካፀደቃቸው ሕግጋት አንዱ፣ የተመሠከረላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲቲዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን ነበር።