BRIDGE Research & Innovation - Parliaments. Peace. Policy

የብሪጅ ዳሰሳዊ ምልከታ፡ የመስክ ስራዎች

የኢትዮጵያ እንደራሴዎች፣ ወደ ‘ምርጫ ወረዳዎቻቸው በመሄድ፣ ከወከሏቸው መራጮቻቸው እና በየአካባቢዎቻቸው ከሚገኙ ተቋማት ጋር በቀጥታ በመገናኘት የመስክ ጉብኝቶችን አድርገዋል። በዚኽ የመስክ ጉብኝቶቻቸውም፣ በሄዱባቸው አካባቢዎች ስለተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን እና ተግዳሮቶችን በመገምገም ተጨባጭ መረጃ ማግኘት ችለዋል።

የብሪጅ ዳሰሳዊ ምልከታ፡ በአዋጅ ቁጥር 1373/2017 ላይ የተደረገ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግሥቱ በክልሎቹ ውስጥ ጣልቃ የሚገባበትን ነባር አዋጅ አሻሽሏል። ምክር ቤቱ፣ መጋቢት 23 2017 ዓ.ም. ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የቀረበለትን ይኽንኑ የማሻሻያ አዋጅ ያፀደቀው በኹለት ድምጸ-ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ ሲሆን፤ ነባሩን አዋጅ ቁጥር 359/1995ን ተክቶ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 በሚል አፅድቆታል።

English